ሆ.ቱ.ስ.ማ.ማ ጥር 8/2013 ዓ.ም የሆቴልና ቱሪዝም ሥራ ማሰልጠኛ ማዕከል ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የቱሪዝም ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ቡዜና አልከድር እና የቱሪዝም ዘርፍ ባለሙያዎች በተገኙበት የስድስት ወር አፈፃፀም ግምገማ አካሄደ፡፡
ክብርት ወ/ሮ ቡዜና በመክፈቻ ንግግራቸው በቱሪዝም ዘርፍ የተዘጋጀው ይህ መድረክ የመጀመሪያ መሆኑንና በስራ፣ በዕቅድ እና የእቅድ አፈፃፀምን እየገመገሙ ስራዎችን በውጤት መሻገር እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡
በበጀት ዓመቱ የሆቴልና ቱሪዝም ሥራ ማሰልጠኛ ማዕከል የስድስት ወር የስራ አፈፃፀም ያቀረቡት አቶ ገዛኸኝ አባተ እና በባህልና ቱሪዝም ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አማካሪ አቶ ይስፋልኝ ሀብቴ አቅርበው ውይይት ተካሂዶበታል፡፡
ውይይቱ በዋነኝነት የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የሚረዳ ዕቅድ ክንውንን መገምገምና ውጤትን መሰረት የክትትልና ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ማስቻልነው፡፡
ይህ የቱሪዝም ዘርፍ መድረክ ከግምገማ ባሻገር በባለሙያዎች የተዘጋጁ የተለያዩ ሰነዶች ቀርበው ውይይት የሚካሄድባቸው ሲሆን ስብሰባው ነገ ጥር 9/2013 የሚጠናቀቅ ይሆናል፡፡