መጋቢት 29/2013 ዓ.ም ሆ/ ቱ/ ሥ/ ማ /ማ
የሁለተኛ ዓመት የቱሪዝም ትምህርት ክፍል ሰልጣኞች ስለ ሐረማያ ሀይቅና በባቢሌ ስለሚገኙ የቱሪስት መዳረሻ ስፍራዎች ስልጠና ተሰጣቸው።
ስልጠናውን የሰጡት የቱሪዝም ትምህርት ክፍል መምህር ማሩ እማኙ እንደተናገሩት የሐረማያ ሀይቅ ከአሥር ዓመት በፊት የደረቀ እንደነበርና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ተፈጥሯዊ እንክብካቤ ተደርጎለት ሐይቁ መልሶ ማገገም መቻሉን አስረድተዋል፡፡
በሀገራችን በሁሉም አከባቢዎች ችግኝ የመትከል መርሃ ግብር ተግባራዊ መደረጉ ደርቀው የነበሩ የውሃ አካላት ዳግም መምጣታቸው አንዱ በጎ ማሳያ መሆኑን በሐሮማያ ሐይቅ የታየው እውነታ ምስክር ነው ብለዋል፡፡ በመሆኑም በሐይቁ ላይ ኑሯቸውን ያደረጉ አዕዋፋትና እና ሌሎች የውሃ አካላትን ማብራሪያ አድርገዋል።
ባቢሌ ከተማ ከሀረር በ40 ኪሎ ሜትር የምትገኝ ሲሆን ከከተማው በአራት ኪሎ ሜትር ርቀት በእሳተ ገሞራ ፍንዳታ ምክንያት የተፈጠሩ የተለያዩ የድንጋይ ቅርጾች ምክንያት ልዪ ስሙ ደኮታ ስለተባለው ቦታም ሰፊ ማብራሪያ መምህር ማሩ ተሰጥተዋል።
በተጨማሪም የግመል ገበያ የሚደረግበትን ቦታ በማየትና በአካባቢው ስለሚገኙ ዕጽዋት ገለጻ ተደርጓል፡፡ ቀጣይ ጉዟችን ወደ ሀረር ነው፡፡ መልካም ጊዜ!