ታህሳስ 16/2015 ዓ.ም ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ቱሪዝም ዘርፍ የቴክኒክና ሙያ የስልጠና አተገባበር፣ የስልጠና ጥራት እና ከሰልጣኝ አመላመል ጀምሮ ያሉ ክፍተቶች እንዲሁም በጥናቱ የተጠቀሱት የተግባር ልምምድ ቦታ እጥረት፣ በቂ የስልጠና ቁሳቁስ አለመኖር፣ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ክፍተት በጥናቱ ተመላክቷል፡፡

እነዚህ ክፍተቶችን ለመሙላት በዝርዝር ከቀረቡ የጥናቱ ግኝቶች በመነሳት አጥኚው ቡድን የሚከተለውን ምክረ ሃሳብ አቅርበዋል፤ የጥራት ማረጋገጫ(quality Assurance)፣ ክፍል እንዲኖር ማድረግ፣ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት መሰረተ ልማት ማሟላት፣
የተግባር ተኮር የልምምድ ቦታዎችን ከግል ሴክተሩ ጋር በመቀናጀት የትብብር ሥልጠናዎችን ማመቻቸት፤ በቴክኖሎጂ የተደገፉ ሥልጠናዎችን መስጠት የሚያስችሉ ሥራዎችን መስራት ይጠበቃል የሚል ምክረ ሃሳብ የጥናት ቡድኑ አስተባባሪ እና የጥናቱ አቅራቢ የኢንስቲትዩቱ አሰልጣኝ እታፈራሁ ሲሳይ አቅርበዋል፡፡
ጥናቱን ተመርኮዞ ከተሳታፊዎች የተለያዩ ሃሳቦች ቀርበው ውይይት ተካሂዶባቸዋል፡፡ የሥራና ክህሎት ሚ/ር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ተሻለ በሬቻ የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ እና የጥናትና ምርምር ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ይታሰብ ስዩም ከተሳታፊዎች ለቀረቡ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ለጥናቱ ተጨማሪ ግብዓት የሚሆኑ መረጃዎች የተገኙበት እንደሆነ ገልጸው ምላሽም ሰጥተዋል፡፡