ቱ.ማ.ኢ ሰኔ 28/2014 ዓ.ም አዲስ የተሾሙ አመራሮችና የቀድሞ የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ከማኔጅመንት አባላቱ ጋር ይፋዊ ተውውቅና የስራ ርክክብ አደርገዋል፡፡
የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ቀድሞ ከነበረበት የሆቴልና ቱሪዝም ማሰልጠኛ ማዕከል ወደ ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ሲያድግ በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ ሥልጠና በመስጠት ለሀገራችን የመጀመሪያ እንደመሆኑ አሁንም የተሰጠውን ተልእኮ በብቃት ይወጣ ዘንድ በአዲስ መልክ በሶስት ምክትል ዋና ዳይሬክተር እና በአንድ ዋና ዳይሬክተር ተደራጅቷል፡፡

ወደ ተቋሙ የተቀላቀሉት የሥራ ኃላፊዎች ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ ዋና ዳይሬክተር (የቀድሞው የቴክኒክና ሙያ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር)፣ አቶ ሃብታሙ ክብረት ም/ ዋና ዳሬክተር (በቀድሞው ቴክኒክና ሙያ ኤጀንሲ ም/ዋና ዳይሬክር) እና የተቋማችን ቦርድ አባል የነበሩ፣ አቶ ገዛኸኝ አባተ የተቋማችን ም/ዋና ዳይሬክተር አሁንም በቦታቸው ያሉ፣ አቶ ይታሰብ ስዩም ም/ዋና ዳይሬክተር፣ በተቋማችን ከ10ዓመት በላይ የሆቴል መምህር እና የገነት ሆቴል ሥራ አስኪያጅ ሆነው በማገልገል ላይ የነበሩ ናቸው፡፡ እነዚህ አመራሮች ካላቸው የሥራ ልምድና የሙያ ስብጥር አንፃር ለተቋሙ ዕድገት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ያበረክታሉ ተብሎ የታመነባቸው ናቸው፡፡
ተቋሙ በርካታ ወጣቶችን በሆቴልና በቱሪዝም ዘርፍ በአጫጭር ፣በደረጃ፣ በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግሪ ሥልጠና የሥራ ዕድል ተጠቃሚ ማድረግ የሚያስችል ከመንግስትም ከፍተኛ ኃላፊነት የተጣለበት የማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ነው፡፡
በዛሬው ዕለት የስራ ርክክብ ያደረጉት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ሆነው ላለፉት ሶስት ዓመት ተኩል ሲያገለግሉ የቆዩት ወ/ሮ አስቴር ዳዊት ለአዲሶቹ አመራሮች ለነባሮቹም እንዲሁም ለማኔጅመንት አባላቱ የመውጪያ ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን በጅምር ያሉ ስራዎችን እና የተቋሙን የ53 ዓመት ዋናዋና ጉዞዎች አስተዋውቀዋል፡፡
የተቋሙ አመራሮችና የማኔጅመንት አባላቱም ለወ/ሮ አስቴር ያላቸውን አክብሮትና መልካም የስራ ጊዜ ተመኝተዋል፡፡ ወ/ሮ አስቴር ዳዊት በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ም/ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተመድበዋል፡፡