ሆ.ቱ.ሥ.ማ.ኢ ግንቦት 01/2011 ዓ.ም የሆቴልና ቱሪዝም ሥራ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ለመማር ማስተማር ሂደትና ለተመራማሪዎች በቂ ክምችት እንዲኖር ለማድረግ የቤተመጽሐፍቱን አገልግሎት ለማሻሻል እየተሰራ መሆኑን የኢንስቲትዩቱ የቤተመጽሐፍት ኃላፊ አቶ ይሄነው አንማው ገለጹ፡፡
ኃላፊው አቶ ይሄነው እንዳሉት በኢንስቲትቱ በቤተ መጽሀፍቱ የኢ-ላይብረሪ አገልግሎቶችን ለመጀመር የኢንተርኔት ዝርጋታና ሌሎች አስፈላጊ ግብዓቶች አየተሟሉ መሆኑን ገልጸው አጋዥ መጽሐፍትን ለማከማቸት በተሰራው ስራ በሃርድና በሶፍት ከፒ ብዙ መጽሐፍት እንደተደራጁ ገልፀዋል፡፡ በቅርቡም በቱሪዝምና ቋንቋ ዘርፍ ለሰልጣኞች አጋዥ የሚሆኑ 240 መጽሀፍት ከብሔራዊ በመዛግብትና ቤተ መጽሐፍት ኤጀንሲ ለተቋሙ ተበርክቷል ብለዋል፡፡
አሁን በተቋሙ የሰልጣኞችን የንባብ ባህል ለማዳበር ከመምህራን ጋር ተባብሮ መስራት እንደምጠበቅም አቶ ይሄነው አንማው መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
በቤተ-መፅፍቱ ውስጥ ዓለም አቀፍ ይዘት ያላቸው ከ6000 በላይ አጋዥ መጽሀፍት ይገኛሉ፡፡