ቱ. ማ. ኢ ግንቦት 9/2014 ዓ.ም የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩትና የሸራተን አዲስ ሆቴል አብሮ ለመስራት በተገባው ስምምነት መሰረት የሆቴል ሰልጣኞች ትምህርታዊ የተግባር ጉብትኝት አድርገዋል፡፡

ይህንን የተግባር ስልጠና የሆቴሉ ዋና ሥራ አስኪያጅ ጨምሮ ከፍተኛ ኃላፊዎች በተገኙበት እንዲጀመር ተደርጓል፡፡ በተጨማሪም ለሰልጣኞች የማነቃቂያ ንግግር በማቅረብና አንጋፋና ወጣት የሆቴሉ ባልደረቦች የሥራ ላይ ተሞክሯቸውን አካፍለዋል፤ ዋና ዋና የሆቴሉ ሥራ ክፍሎችም ተጎብኝተዋል፡፡
ይህ የተግባር ስልጠና ቀጣይ እንደሚሆንና ከሆቴሉ ጋር አብሮ እንደሚሰራ የሆቴሉ ስልጠና ክፍል ኃላፊ ሚስተር አንቶንኒ ገልጸዋል፡፡
የሸራተን ሆቴል ላደረገው አቀባበልም የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት አካዳሚክና ምርምር ዲን አቶ አብርሃም ለገሠ የምስጋና ሰርተፊኬት አበርክተዋል፡፡
ከዚህ ጋር በተያያዘ በዚህ ሳምንት የሀያት ሬጀንሲ ትምህርታዊ ጉብኝት እና የተግባር ልምምድ በሆቴሉ የሚጀምሩ ሰልጣኞች የትውውቅና የጉብኝት ፕሮግራም ተካሂዷል፡፡
ሃያት ሪጀንሲ ሆቴል ከዚህ ቀደም የመግባቢያ ሰነድ በመፈራረም 60 ሰልጣኞችን ተቀብሎ በሳምንት ሶስት ቀን የተግባር ልምምድ ሥልጠና በመስጠት ለሰልጣኞቻችን ትልቅ እድል የሰጠ አጋራችን በመሆኑ ለሆቴሉ የሥራ ኃላፊዎችና ለዋና ስራ አስኪያጁ ሚስተር ሄዶ በዚህ አጋጣሚ ምስጋና እናቀርባለን፡፡