የኢንስቲትዩቱ ሠራተኞች አቅም ግንባታ ስልጠና ወሰዱ
የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት አመራርና ሠራተኞች የአቅም ግንባታ ሰልጠና እና የESTRIP ፕሮጀክት ትውውቅ አደረጉ።
በፕሮግራሙ መክፈቻ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ ባስተላለፉት መልእክት ESTRIP ፕሮጀክት ውጤትን መሰረት ያደረገ አፈፃፀም የሚፈልግ እና ከኢንድስትሪው ጋር በጣም የተሳሰረ የበቃ የሰው ሃይል እንዲኖር የሚያደርግ በመሆኑ በአገባቡ መምራት ይጠበቅብናል ብልዋል፡፡
የኢንስቲትዩቱ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ አባተ በበኩላቸው እንደተናገሩት በሁለት ቀን ቆይታ ከሥራ ጋር በተያያዘ ስልጠና እና ከፕሮጀከት ትውውቅ ባሻገር አዲሱን የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲ እንዲሁም ተቋማዊ የባህል ግንባታ እና ‘የልቦና ውቅር ’ (mindset) የሚሉ ስልጠናዎች መዘጋጀታቸውን ገልጸው ሰራተኛው በትኩረት እንዲከታተል አሳስበዋል፡፡
በመቀጠል የስልጠናና አቅም ግንባታ ዘርፍ ም/ዋና ዳይሪክተር አቶ ሀብታሙ ክብረት የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲውን አቶ አብርሃም ለገስ ESTRIP ፕሮጀክት በተከታታይ አቅርበዋል፡፡
ተቋማዊ የባህል ግንባታ እና ‘የልቦና ውቅር ’ ስልጠና በዘርፉ ባለሙዎች ተሰጥቷል፡፡
ትክክለኛ መረጃ ለማግኘት የሚከተሉትን ሊንክ በመጠቀም የፌስቡክ ገጻችን ይጎብኙ፣ ላይክ፣ ሼር ያድርጉ
We kindly invite you to join our telegram group https://t.me/tticommunication and like, follow, and share the Facebook page https://www.facebook.com/tticommunication

Recent Comments