ሆ.ቱ.ሥ.ማ.ኢ ሰኔ 15/2011 ዓ.ም የሆቴልና ቱሪዝም ሥራ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ሰራተኞች፣መምህራንና ሰልጣኞች “እኛ ለትውልድ ችግኝ እንጂ ችግርን አናወርስም!” በሚል መሪ ቃል ከሀያ ሺህ በላይ የሚሆኑ ችግኞችን ቦሌ አትላስና የአውሮፓ ህብረት አካባቢ ተከሉ፡፡
በመሃግብሩ ላይ የተገኙት የቦሌ ክ/ከተማ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ጥላሁን ችግን መትከል ለሀገራችን ኢኮኖሚ ትልቅ ድርሻ አለው፣ የኢንስቲትዩቱ ማህበረሰብም ችግኞችን በመንከባከብ ለቀጣይ ትውልድ ማሸጋገር አለበት ብለዋል፡፡የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ አስቴር ዳዊት ይህ የችግኝ ተከላ መርሃግብር የተቋሙ 50ኛ ዓመት እየተከበረ ባለበት ወቅት መሆኑ ታሪካዊነቱ የጎላ ነው ያሉት ለሚተከሉ ችግኞችም አስፈላጊው እንክካቤ እናደርጋለን ብለዋል፡፡

Recent Comments