የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ሰራተኞች በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል።የኢንስቲትዩቱ ሰራተኞች የብልጽግና ሁለተኛ ጉባኤ ላይ በተለይ በቱሪዝም ዘርፉና የሥራ ዕድል ፈጠራ ጋር በተያያዘ እንዲሁም በሀገር አቀፍ ደረጃ ፓርቲው ያወጣቸውን አስር የትኩረት መስኮች መሰረት በማድረግ ምክክር አድርገዋል።በመድረኩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ መንግስት ገለልተኛና ውጤታማ ሲቪል ሰርቫንት እንዲኖር የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው ብለዋል። በሌላም በኩል ለጠንካራ ሀገረ መንግስት ግንባታ ሲቪል ሰርቪሱ የማይተካ ሚና እንዳለው በመግለጽ ኢንስቲትዩቱ ተልዕኮውን መሠረት ያደረገ ስልጠና፣ጥናትና ምርምር በማካሄድ ዜጎች የሥራ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ እየሠራ መሆኑን ተናግረዋል።የውይይት ሰነድ ያቀረቡት የኢንስቲትዩቱ ስልጠናና አቅም ግንባታ ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ክብረት የሰላም ግንባታ፣ የሀገር ግንባታ፤ የኢኮኖሚ ልማትን ማፋጠን፣ ውጤታማ ዲፕሎማሲ፣ የሚዲያና ኮሚኒኬሽን የሚሉ10 ነጥቦች ቀርበው ውይይት ተደርጓል።የውይይቱ ተሳታፊዎች በተለይ ከሰላም ግንባታ ከኢኮኖሚ ልማት እንዲሁም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩቱ እየሰራ ከሚገኘው ሥራ አንጻር ያላቸውን ምልከታ ገልጸዋል።ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ

ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et