ቱ ማ ኢ ሚያዝያ 16/2017 ዓ ምየቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት አሰልጣኞች በጅማ ከተማ የሚገኙ የቱሪስት መዳረሻዎችን ጎብኝተዋል። የማሰልጠኛ ኢንስቲትዩቱ ጉዞ አስተባባሪዎች መምህር ዮናስ ቶሎሳ እና መምህር ታከለ ኛሜ እንደገለጹት ይህ የተግባር ስልጠና ጉብኝት ለአሰልጣኞች ህብረት የሚያጠናክር ፣ የኢንዱስትሪው እውቀት ኖሯቸው ለሰልጣኞች ስለ ሀገራቸው ሙሉ መረጃ እንዲሰጡና የተሟላ እውቀት እንዲኖራቸው የሚያደርግ ነው ብለዋል።ሌላው በንድፈ ሀሳብ የሚያስተምሩትን ትምህርት ተግባር ተኮር እንዲያደርጉ የሚረዳ፤ በተጨማሪም በመንግሥት የተሰሩ የቱሪዝም ሳይቶች በመጎብኙታቸው በቀጣይ ለጥናትና ምርምር ሥራዎች የሚረዳ መሆኑን አስተባባሪዎቹ ገልጸዋል።

የጅማ ከተማ ሙዚየም ከ1800 ዓ ም እስከ 1933 ዓ ም ድረስ አምስት ነገስታት የተጠቀሙበት ቁሳቁስ፣ ባህላዊ ጌጣጌጦች፣ ከጣሊያን የተወረሱ ዘመናዊና ባህላዊ የጦር መሳሪያዎች ፣ፎቶ ጋላሪዎች፣ የእንስሳት ቅሬተ አካል እንደሚገኙ የሙዚየሙ አስጎብኚዎች ስረድተዋል።
በተጨማሪም በሙዚየሙ 429 ሲኒ የያዘ ረከቦትና ለሁሉ የሚበቃ ጀበና እንደሚገኘ ተገልጿል ።
በተጨማሪም ሰቃ ፏፏቴ እና እድሳት ላይ የሚገኘው 195 ዓመት ያስቆጠረው የንጉስ አባጅፋር ቤተመንግሥት እና በከተማው የተሰሩ የኮሪደር ልማቶች ተጎብኝቷል።
ጉብኝቱ ቀጣይ ቀናትም በሌሎች አከባቢ የሚቀጥል ይሆናል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et