መጋቢት 15/2015 ዓ.ም ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ አየር መንገድ አቪየሺን ዩንቨርስቲ ጋር በመተባበር ለሁለት ቀናት በአመራርና አስተዳደር ዙሪያ ለኢንስቲትዩቱ የማኔጅመንት አባላት ስልጠና ሰጥቷል።
በስልጠናው ማጠቃለያ መልዕክት ያስተላለፉት የተቋሙ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ይታሰብ ስዩም ስልጠናው ተቋማዊ ለውጥ ለማምጣት የሚያስችል እንዲሆን ሁሉም ኃላፊነት እንዳለበት ጠቁመው፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ካለው የሥራ ዲሲፕሊን እና ከገነባው ጠንካራ ስም አንፃር ስልጠናውን መውሰዳችን ጠቀሜታው የጎላ ነው ብለዋል።
ኢንስቲትዩቱ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር የረጅም ጊዜ የሥራ ግንኙነት እንዳለው ይታወቃል።
Recent Comments