ጥር 15/2014 ዓ.ም የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በ2014በጀት ዓመት የመጀመሪያ የስድስት ወር ዕቅድ አፈፃፀም የተቋሙ አመራሮች፣ መምህራንና ሰራተኞች በተገኙበት ተገምግሟል።
ኢንስቲትዩቱ ከመደበኛ የማሰልጠን፣ የማማከርና የምርም ሥራዎች እና ከማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት ባሻገር በስድስት ወር አፈፃፀሙ በርካታ ሥራዎች መሠራታቸው የተገለጸ ሲሆን በተለይም በሲዳማ ክልል የዓለም ቱሪዝም ቀን መከበርን አስመልክቶ የክልሉን 31 ዓይነት ባህላዊ ምግብ ሳይንሳዊ በሆነ ደረጃ በማውጣት የተሰራው ለሆቴሎች በሚቀርብ ሜኑ ማዘጋጀት መቻሉ፤ የክልሉን የቱሪስት ቆይታ ማራዘም የሚያስችል ቱር ማፒንግ እና የጥቅል ጉዞ መዘጋጀቱ፤
በክልሉ ያሉ የአስጎኝ ድርጅቶች እና የሆቴል ማናጀሮች የማነቃቂያ ስልጠና መሰጠቱ፣ የሸገር ፕሮጀክት የወንዞች ዳር ልማት ከአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ጋር የተሰሩ ሥራዎች ተቋሙን ከፍ ባለደረጃ ማስተዋወቃቸው ፣ ከተለያዩ ተቋማት ጋር የተሰሩ የአጫጭር ስልጠናዎች ፣ ለመምህራን እና ለሰልጣኞች የተሰጡ የማነቃቂያ ሥልጠና፤ በአገራዊ ጉዳዮች ላይ የነበረው ከፍተኛ አስተዋጽኦ፤ በዘርፉ ለክልሎች የተሰጠው ሥልጠና በጥንካሬ የታዩ ናቸው።
በሌላም በኩል ተቋሙ ከዕቅድ አንፃር ያልተከናወኑ ሥራዎች አለመከናወናቸው በድክመት ታይቶበታል።
Recent Comments