ቱ.ማ.ኢ ግንቦት 01/2017 የኢትዮጵያ ቱሪስት አስጎብኚዎች ማህበር አባላት ለቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ቱሪዝም ሰልጣኞች ተሞክሯቸውን አካፈሉ። በአስጎብኝኘት የረጅም ዓመታት ልምድ ያላቸው ባለሙያዎች ለቱር ጋይድ፣ ቱር ኦፕሬሽን የደረጃ እና ቱሪዝም ማኔጅመንት ድግሪ ሰልጣኞች ወቅታዊ የሀገራችን ቱሪዝም ሁኔታን በሚያስረዳ እና ሰልጣኞች ወደፊት እንዴት ስራ መጀመር እንደሚችሉ ከተሞክሮአቸው ስልጠና ሰጥቷል። ይህ ስልጠና በትምህርት ላይ የሚገኙ ሰልጣኞች በአስጎብኝነት ላይ ከሚሰነዘሩ አሉታዊ አስተያየቶች ባሻገር በሙያው ላይ ተስፋ እንዲኖራቸው እንደሚያደርግ አሰልጣኝ አብይ ንጉሴ ገልጸዋል ።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et

Recent Comments