በጣሊያን አገር የታወቁ ሼፎች ለተቋማችን ፤ የፔስትሪና ፎሬን ዲሽ የ2ኛ ዓመት ሰልጣኞች የጣሊያን ሀገር ባህላዊ ምግብ አሰራር ስልጠና ትናንት በኢትዮጵያ የጣሊያን ኤምባሲ በተደረገ ውድድር ተጠናቀቀ፡፡
ውድድሩ በሥልጠናው ተሳታፊ ከነበሩት12 ሰልጣኞች መካከል ስምንቱ ለውድድር የቀረቡ ሲሆን በሁለት ቡድን ተከፍለው ኦሪቼቴ (ORECCHIETTE) እና ሪዞቶ ( RISOTTO ) የተባሉ የጣሊያን ምግቦችን ሰርተዋል፡፡ ዳኞቹ ከማማሚያ ሪስቶራንት፣ ጉስቶ ሪስቶራንት እና ሊንዳ ሪስቶራንት ሲሆኑ አሸናፊ የሆኑት ቡድኖች ከነዚህ ሪስቶራንቶች የተግባር ልምምድ እንዲያገኙ እድል ተመቻችቶላቸዋል፡፡