ቱ.ማ.ኢ ጥር 2015 ዓ.ም ሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከሲዳማ ክልል ጋር በመተባበር ባዘጋጀው ኤግዚቢሽንና ባዛር ላይ የተገኙ ጎብኚዎችቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የሚሰጠውን ስልጠና ወደ ክልሎች አውርዶ ቢሰራ ህብረተሰቡ ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገልጸዋል።

ጎብኚዎቹ እንደገለጹት በአጫጭር ስልጠና፣ በማታና ቅዳሜና እሁድ ስልጠናዎችን ለመከታተል በአቅራቢያችን ቢገኝ ጥሩ ነበር፤ ፍላጎቱ እያለን አማራጭ አላገኘንም ብለዋል።
ኢንስቲትዩቱ የልህቀት ማዕከል በማድረግ ወደ ክልሎች ወርዶ በሀገሪቱ የሚገኙ የቱሪዝምና ሆስፒታሊቲ ዘርፍ ሥልጠና የሚሰጡ ማሰልጠኛ ፖሊ ቴክኒኮችን መደገፍ እና ማብቃት ላይ እንዲሰራ መንግስት ልዩ ትኩረት ሰጥቶት እየሰራ ነው።