የካቲት 18/2013 ዓ.ም የሆቴልና ቱሪዝም ሥራ ማሰልጠኛ ማዕከል የቱሪዝም መምህራንና በደብረብርሃን ዩንቨርሲቲ ቱሪዝም መምህራን መካከል የጋራ የእርስ በእርስ ስልጠና ተካሄደ፡፡
ከዚህ በፊት ከደብረብርሃን ዩንቨርሲቲ ጋር አብሮ ለመስራት በተደረገው ስምምነት መሠረት ወደ ተግባር ስራ በመገባት የመምህራን የእርስ በእርስ ስልጠና እና ቀጣይ ፕሮጀክት ዙሪያ ሊሰሩ ስለሚገባቸው ስራዎች የስራ አቅጣጫ ተወስዷል፡፡
ከእርስ በእርስ ስልጠናው ከሁለቱ ተቋማት የተወጣጣ ቡድን የተዋቀረ ሲሆን ቡድኑ የቀጣይ ሥራ መነሻ ዕቅድ በፍጥነት እንዲያዘጋጅ የሆቴልና ቱሪዝም ሥራ ማሰልጠኛ ማዕከል የምርምር ክፍል ሃላፊ አቶ ማዘንጊያ ሽመልስ አቅጣጫ ሰጥተዋል፡፡ ፡፡
ከደብረብርሃን ዩንቨርሲቲ የመጡ መምህራን በተቋሙ የሚገኙ የተግባር ስልጠና የሚሰጥባቸውን ክፍሎችም ጎብኝተዋል፡፡
Recent Comments