የልዑካን ቡድኑ ኢንስቲትዩቱን በጎበኙት የካርሎስ ኢንተርናሽናል ፐብሊክ ቻርተር ስኩል ዳይሬክተር አሊሰን ኮኮሮስ ባዩት ነገር ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
የኢንስቲትዩቱን የተግባር ስልጠና ክፍሎች ፣የእንግዳ አቀባበልና የምግብ ዝግጅት ክፍል ጎብኝተዋል፡፡ ከተቋሙ ጋር ለሚኖረን ግንኙነትና ለቀጣይ ሥራዎች የሚረዱ የመረጃ ልውውጥም ተደርጓል፡፡
ካርሎስ ሮዛሪዮ ኢንተርናሽናል ስኩል በአሜሪካን አገር ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ 50 ዓመታትን ያስቆጠረ ሲሆን በእንግሊዝኛ ቋንቋ ለጎልማሶች ለሆስፒታሊቲ ኢንደስትሪ እና ለሌሎች በርካታ የትምህርት መስኮች የቋንቋ ስልጠና በመስጠት ረጅም ልምድ ያካበተ ነው፡፡
Recent Comments