ቱ. ማ .ኢ የሆቴል ዘርፍ ሰልጣኞች የተግባር ስልጠና በሆቴሎች እየተሰጠ ነው

የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የአንደኛ አመት ሁለተኛ ስሚስቴርና ሁለተኛ ዓመት አንደኛ ስሚስቴር የሆቴል ሰልጣኞች የተግባር ስልጠና በተለያዩ ሆቴሎች እየተሰጣቸው ነው፡፡
እነዚህ ለተግባር ስልጠና ለማድረግ የወጡ ሰልጣኞች ያሉበትን ደረጃ የሚከታተል ስድስት ቡድን ተዋቅሮ ክትትል እያደረጉ ነው፤ ይህንን ቡድን ለሥራ ለማሰማራት በተገኙበት ወቅት የተቋሙ የስልጠናና አቅም ግንባታ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ክብረት እንደተናገሩት በ52 ሆቴሎች ከአራት መቶ በላይ ተማሪዎች መሰማራታቸውን ገልጸው እነዚህን ሰልጣኞች በተመደቡባቸው ሆቴሎች ውስጥ በስልጠና ዘርፋቸው ስለመመደባቸው ክትትል ተደርጓል፡፡
ክትትል ከተደረገባቸው ሆቴሎች መካከል ሳሬም ሆቴል፣ ኢትዮጵያ ሆቴል፣ አላአ ሆቴል እና ሳፋየር ሆቴሎች ውስጥ ያሉ ሰልጣኞችን በሰለጠኑበት ሙያ ስለመመደባቸው እና ሆቴሎቹ በቂ ግንዛቤ በመስጠት ሰልጣኞች ከራሳቸው የሚጠበቀውን ብቃትና ክህሎት ማሟላታቸውን እና ባለሆቴሎችም በሰልጣኞች ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
ትክክለኛ የኢንስቲትቱን መረጃዎችን ለማግኘት የኢንስቲትዩቱን
ፌስቡክ ገጽ https://www.facebook.com/tticommunication ወይም
ቴልግራም https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት https://www.tti.edu.et/ ይጎብኙ