“ሴቶችን እናብቃ ልማትና ሰላም እናረጋግጥ” በሚል መሪ ቃል ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ተከበረ፡፡

በቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት “ሴቶችን እናብቃ ልማትንና ሠላም እናረጋግጥ” በሚል መሪ ቃል የተከበረውን ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን አስመልክቶ የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ አስቴር ተክሌ መልዕክት አስተላልፈዋል
ወ/ሮ አሰቴር እንደገለጹት የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎን ለማረጋገጥ፣እና በፓለቲካው ና በኢኮኖሚው መስክ በብቃት ተሳትፎ እንዲኖራቸው ለማስቻል ሁሉም ሃላፊነቱን መወጣት እንዳለበት ገልጸው ፤ ከማሕበረሰቡ ጋር አብሮ የዘለቀ የሃገር ግንባታ ድርሻቸውን እንዲወጡ ተቋሙ የተለያዩ ስልጠናዎችን በመስጠት እያበረታታ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ113ኛ ጊዜ እንዲሁም በሀገር አቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ48ኛ ጊዜ የተከበረውን ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ማርች 8“ ን አስመልክቶ የተቋሙ ከፍተኛ የምርምር ባለሙያ ዶ/ር ታግሎ ካሳ ሴቶች ወደ አመራርነት ሲመጡ ምን ዓይነት ስልቶችን መጠቀም እንዳለባቸው ፖለቲካዊ ፣ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተሳትፎን ከማሳደግ አንፃር ግንዛቤ የሚያስጨብጥ ስልጠና ሰጥተዋል።
የኢንስቲትዩቱ አንጋፋ አሰልጣኝ ወ/ሮ አንለይ ሙሉጌታ የህይወት ልምዳቸውን አካፍለዋል፡፡
ትክክለኛ የኢንስቲትቱን መረጃዎችን ለማግኘት የኢንስቲትዩቱን
ፌስቡክ ገጽ https://www.facebook.com/tticommunication ወይም
ቴልግራም https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት https://www.tti.edu.et/ ይጎብኙ