በአገራችን ለ34ኛ ጊዜ በሲዳማ ክልል በሀዋሳ ከተማ በደማቅ ሁኔታ ይከበራል።በዓሉ መስከረም 14እና 15 /2014ዓ.ም የበተለያዩ ዝግጅቶች የሚከበር ሲሆን

ተቋማችን በዓሉን ምክንያት በማድረግ ወደክልሉ ለሚመጡ እንግዶች የተሻለ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ሥልጠና ከሁለት ሣምንት በፊት ሀዋሳ ከተማ የሚገኙ የሆቴል ባለቤቶችና ሥራ አስኪያጆች እንዲሁም አስጎብኝ ዎች ድርጅቶች ሥልጠና ሰጥቷል።
ኢንስቲትዩቱ በሲዳማ ክልል የሚገኙ የተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ የሆኑ የቱሪስት መስህብ ሥፍራዎችን፣ ባህላዊ ዕሴቶችን ማስተዋወቅና የጎብኝዎችን የቆይታ ከአንድ ቀን እስከ ሰባት ቀን። ማራዘም የሚያስችል (Tour package and Tour map) ለመጀመሪያ ጊዜ እበራሱ ባለሙያዎች አዘጋጅቷል። በተጨማሪም የክልሉን ባህላዊ ምግብ ከነአሰራሩ ጭምር በባለሞያ የታገዘ መለያ በማውጣት ክልሉን ሊያስተዋውቅ የሚችል 33 ዓይነት ያለው የሲዳማ ምግብ ሜኑ (የምግብ ዝርዝር) ከክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ጋር በመተባበር የምግብና መጠጥ ዝግጅት ከፍል መምህራን አዘጋጅተዋል። ይህም በዓይነቱ ለየት ያለ ማንኛውም የውጭ አገር እንግዳም ሆነ አገራችን ያሉ የህብረተሰብ ክፍሎች የሲዳማ ባህላዊ ምግብን እንደማንኛውም ምግብ በሚስተናገዱበት ሆቴል አዘው እንዲመገቡት የሚያስችል ዓለም አቀፍ ደረጃ ያለው የምግብ ዝርዝር ነው።
የዓለም ቱሪዝም ቀን “ቱሪዝም ለሁለንተናዊ ዕድገት “በሚል መሪ ቃል የሚከበር ሲሆን የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴርና ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር፣ የተጠሪ ተቋማት ኃላፊዎችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።