በመክፈቻ መርሃ ግብሩ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚልን ጨምሮ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ ዓለም አቀፍ ተሳታፊ እንግዶች እና የዘርፉ ተዋንያን በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ፡፡
የዘንድሮ የዓለም ኢንተርፕረነርሺፕ ሳምንት ከ200 በላይ በሆኑ ሀገራት በጋራ እንገንባ/together we build) በሚል መሪ መልዕክት ይከበራል፡፡ በሳምንቱ የፈጠራ ባለሙያዎችና የሥራ ፈጣሪዎች የሚበረታቱበት፣ አዳዲስ የንግድ ሥራዎች የሚደገፉበት፣ ተሞክሮና ልምድ የሚለዋወጡበት፣ ትስስር የሚፈጥሩበት እና እውቅና የሚያገኙበት የተለያዩ መርሃ ግብሮች ይካሄዳሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et


Recent Comments