መጋቢት 30/2015 ዓ.ም የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ዕቅድ አፈፃጸም ሲገመገም በርካታ ተግባራት የተከናወኑ ሲሆን ከማዕቀፍ ግዢ ጋር የተያያዙ ክፍተቶች እና የ2015 ዓ.ም የአዳዲስ ሰልጣኞች ቅበላ መዘግየት የዘጠኝ ወር ዕቅድ አፈፃጸማችንን ሙሉ ለሙሉ እንዳናሳካ አድርጎናል ተብሏል፡፡

የተቋሙን የዘጠኝ ወር ዕቅድ አፈፃጸም የዕቅድና በጀት ክትትል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሀይሉ ነገዎ ያቀረቡ ሲሆን በአጫጭር ስልጠና፣በምርምርና የማማከር አገልግሎት እንዲሁም የሪፎርም ሥራዎቻችን በጥንካሬ የሚገለጹ መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡ በሌላ በኩል ተቋሙ መንግስት የግዢ አሰራሩን በዲጅታል ለማድረግ እንደ ሙከራ ከጀመረባቸው ተቋማት ውስጥ የሚገኘው ኢንስቲትዩቱ ከተቋሙ የስልጠና ፍላጎት ጋር አልፎ አልፎ ለተግባር ስልጠና የማይገኙ ግብአቶችንና ቁሳቁሶችን ከግዥና ንብረት አስተዳደር ጋር በመነጋገር እየተፈቱ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን የግዥ ሂደቱ አሁንም በሚፈለገው ፍጥነት እየሄደ አለመሆኑ በሪፖርቱ ተመላክቷል፡፡
በሪፖርቱ ጠንካራ ተብለው የተነሱትን አጠናክሮ መቀጠልና በዘጠኝ ወሩ ውስጥ መከናወን ሲገባቸው ያልተከናወኑትን በቀሪው ጊዜ በልዩ ትኩረት ማከናወን ይጠበቃል፡፡
ሪፖርቱን አስመልክቶ ከተሳታፊዎች ጥያቄዎችና አስተያየቶች የተሰጡ ሲሆን ከአንዳንድ የሥራ ክፍሎች የሚታዩ የቀናነት ችግሮች ሥራን በፍጥነት አለመስራትና የደንበኞች እርካታ በሚፈለገው መጠን እንዳይደርስ ማድረጋቸውን በመገለጫ አስረድተዋል። በተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ላይ የስልጠናና አቅም ግንባታ ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ክብረት እና የጥናትና ምርምርና ማማከር ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ይታሰብ ስዩም ምላሽ የሰጡ ሲሆን ከአዳዲስ ቅበላ ጋር ተያይዞ አገር አቀፍ ጉዳይ በመሆኑ ከግምት ውስጥ ገብቶ አሁን የተቀበልናቸውን አዳዲስ ሰልጣኞች ስልጠና እንዲጀምሩ ማድረግ፣ በዘርፉ የሥራ እድል መፍጠርና ለዚህም አስፈላጊ ግብዓቶችን ማሟላት፣ ሥራዎችን በቀናነት ማከናወን፣ የሰራተኞችን የስራ ከባቢ ምቹ ማድረግና የኑሮ ውድነትን ለማቅለል በተቋማችን የተጀመሩ ሥራዎችን በፍጥነት ማከናወን፤ እንዲሁም የተጠያቂነት ሥርዓትን ማስፈን በትኩረት የምንሰራቸው ተግባራት ናቸው ሲሉ የተቋሙ የአመራርና አስተዳደር ዘርፍ ም /ዋና ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ አባተ ከቀረበው ሪፖርት ከተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ተነስተው አቅጣጫ ሰጥተው አጠቃለዋል፡፡