መስከረም15/2016 ዓ ም የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ሥራና ክህሎት ሚኒስተር ጋር በመተባበር ላለፉት አስራ አምስት ቀናት ሲዘጋጅ የቆየው የቱሪዝምና የሆቴል ዘርፍ የደረጃ ሶስትና አራት ማስተማሪያ ሞጁሎች ዝግጅት ተጠናቀቀ፡፡
ማጠቃለያውን አስመልክቶ የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የስልጠናና አቅም ግንባታ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ክብረት እንደገለጹት በሞጁል ዝግጅቱ ላይ የተሳተፉ አሰልጣኞችንና አስተባባሪዎችን በማመስገን በዚህ አጭር ጊዜ የሚያኮራ ሥራ በመስራታችሁ ልትኮሩ ይገባል ብለዋል፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስተር የስርዓተ ስልጠና እና ማሰልጠኛ መሳሪያዎች ዝግጅት ዴስክ ኃላፊ ወ/ሪት ትዕግስት ከበደ በበኩላቸው የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት አሰልጣኞችና ከሌሎች የቱሪዝምና ሆቴል ማሰልጠኛ ተክኒክና ሙያዎች የተወጣጡ ባለሙያዎች በደረጃ ሶስትና አራት በስምንት ሙያዎች 114 ሞጁሎች እንዲያዘጋጁ ታቅዶ በዚህ አጭር ጊዜ ሰርተው በማጠናቀቃቸው የተሰማቸውን ደስታ በመግለጽ የአሰልጣኞች ምልመላም የተሳካ በመሆኑ ጥሩ ሥራ መሰራቱን ገልጸዋል፡፡
ይህን የማስተማሪያ ሞጁሎች ለ2016 ዓም ትምህርት ዘመን ለማድረስ ትንንሽ እርማቶች ተደርጎ ለክልሎች በቴለግራምና በሲዲ ከደብዳቤ ጋር በማዘጋጀት እንደሚላክ ተናግረዋል፡፡
ይህን የማስተማሪያ ሞጁል ካዘጋጁት አሰልጣኞች መካከል የወላይታ ሶዶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አሰልጣኝ አቶ አበበ መንግስቴ እንደገለጹት በጥሩ መግባባት ሥራውን እደሰሩ
የኢንስቲትዩቱ አሰልጣኝ አቶ ታደሰ ሞላም በዝግጅቱ የተሳተፉ ባለሙያዎች ያበረከቱት አስተዋጾ ቀላል የሚባል እንዳልሆነ ገልጸዋል፡፡
አቶ ፍሬው አበበም ይህንን ሰነድ ተማሪው በቀላሉ የሚያገኙበት መንገድ ቢመቻች ጥሩ ነው በማለት ሀሳባቸውን ሰጥተዋል፡፡
ይህ የማስተማሪያ ሞጁል ዝግጅት በሌሎች ዘርፎችም እንደሚቀጥል ተገልጿል፡፡

Recent Comments