መስከረም 4/2016 ዓ.ም ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ የደረጃ ሶስትና አራት ሞጁል ዝግጅት ተጀምሯል፡፡
የስልጠና ሞጁል ዝግጅቱን ያስጀመሩት በቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የስልጠናና አቅም ግንባታ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ክብረት እንደገለጹት ይህንን የማስተማሪያ ሞጁል በማዕከልነት ለማዘጋጀት ከተለያዩ ክልሎች የተውጣጡ የቱሪዝምና ሆቴል ማሰልጠኛ ተቋማት እና የተቋማችን አሰልጣኞች በደረጃ ሶስትና አራት በስምንት ሙያዎች 114 ሞጁሎች እንደሚያዘጋጁ ተናግረዋል፡፡
አቶ ሃብታሙ ለትምህርት ጥራት በርካታ ግብዓቶች ቢያስፈልጉም የመምህራን አቅም ግንባታ ፣ በጥራት የተዘጋጀ ሰነድ እና ብቃትና ጥራት ያለው አሰልጣኝ መሰረታዊ መሆናቸውን ገለጸዋል፡፡ አክለውም
ይህን ሞጁል የማዘጋጀት ዕድል ያገኛችሁ አሰልጣኞች ልትኮሩ ይገባል በማለት ከዚህ በፊት የነበሩትን በማሻሻልና ያላችሁን አቅምና ልምድ በመጠቀም የሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ የደረጃ ሶስትና አራት ሞጁል በማዘጋጀት ለሀገርና ለትውልድ ጠቃሚ ማድረግ አለባችሁ በማለት የአደራ መለክት አስተላልፈዋል፡፡
በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የስርዓተ ስልጠና እና ማሰልጠኛ መሳሪያ ዝግጅት ዴስክ ኃላፊ ወ/ሪት ትዕግስት ከበደ እንደተናገረችው የሞጁል ዝግጅትን በተመለከተ ሰነዱ በምን አግባብ መዘጋጀት እንደለበትና የሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ ለማሳደግ ይህ ቡድን የሚሰራው ሞጁሉና አስፈላጊ በሆነበት እየተሸሻለ የሚሄደው ካሪኩለም ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ባለፈው ዓመት ደረጃ አንድና ሁለት የማስተማሪያ ሞጁል ተዘጋጅቶ ወደሥራ መገባቱ ይታወሳል።
ውድ የገጻችን ተከታዮች ላይክና ሼር በማድረግ መረጃዎችን ተደራሽ እንድታደርጉልን እንጠይቃለን ።