ታህሳስ 17/2015 ዓ.ም የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የገበታ ለሀገር ፕሮጀክቶች ለሥራ እድል ፈጠራ ያላቸው ፋይዳና የስልጠና ፍላጎትን የሚዳስስ በሚል ርዕስ የጥናት ጽሁፍ በባለሙያዎች፣እና ለዘርፉ ምሁራን አቀረበ፡፡

ጥናቱን ያቀረቡት አሰልጣኝ እና የጥናት ቡድኑ አባል ፍሬው አበበ እንዳቀረቡት ጥናቱ ያተኮረባቸው የኮይሻ፣ ጎርጎራ እና ወንጪ ፕሮጀክቶች ሲሆኑ ፕሮጀክቶቹ ለአካባቢው ማህበረሰብ በቀጥታና በተዘዋዋሪ ሊፈጥሩት የሚችለውን ዝርዝር የቱሪዝም ሥራ ዕድሎች እና የሚፈልጉትን የስልጠና ፍላጎት የሚዳስስ ነው፡፡
እነዚህ መደረሻዎች ለረጅም ዘመናት ያላቸውን እምቅ የቱሪዝም ሃብት ያልተጠቀምንባቸው መሆኑን አንስተው ፕሮጀክቶቹ ለአካባቢዎቹ ከፍተኛ ቱሪስትን የሚስቡ በመሆኑና ከቱሪስት ፍሰቱ ጋር የአካባቢውን ማህበረሰብ በተለያዩ የቱሪዝም የሥራ መስኮች አሳትፎ ተጠቃሚ ለማድረግ እንዲያስችል አማራጭ የሥራ ዕድሎች በጥናቱ የተለዩ ሲሆን በቀጣይ ሊሰሩ የሚገባቸውን ዝርዝር ሥራዎችና የተለያዩ ባለድርሻ አካላት የሚጠበቅባቸውን ተግባርና ሃላፊነት የሚጠቁም ምክረ ሃሳብ በጥናቱ ተመላክቷል።
ገበታ ለሀገር ፕሮጀክቶች በመንግስት ልዩ ትኩረት እየተገነቡ ያሉ አዳዲስ የቱሪስት መዳረሻዎች ናቸው፡፡