እሳት አደጋን ቅድመ ጥንቃቄ ለማድረግ ከተለያዩ ክፍሎች ለተወጣጡ ባለሞያዎች ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ፡፡
የካቲት 25/2014 ዓ.ም የእሳት አደጋን ቅድመ ጥንቃቄ ለማድረግ ከተለያዩ ክፍሎች ለተወጣጡ ባለሞያዎችና ለገነት ሆቴል ሠራተኞች ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በገነት ሆቴል ተሰጠ፡፡
ከእሳት አደጋ ሥራ አመራር ኮሚሽን ቂርቆስ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የአደጋ ስጋት ቅነሳ ጥናትና ትግበራ ባለሞያዎች በተለያዩ ርዕሶች ለሰራተኞች ግንዛቤ ሰጥተዋል፡፡
ስልጠናዎቹም የአደጋ መከላከል፣ የእሳት አፈጣጠር፣ የእሳት አከፋፍል፣የአደጋ ድህንነት ህጎች፣ የእሳት ማጥፍያ መሳሪያዎች አደረጃጀት አፈታተሸ እና አሰራር እንዲሁም መለያ ኮድ ስልጠና የሰጡት የአደጋ ስጋት ቅነሳ ጥናትና ትግበራ ባለሞያዎች ሀና መንግስቱና ምትኩ አበበ ናቸው፡፡
በአንድ ተቋም መሟላት ያለባቸው መሠረታዊ ነገሮች ምንምን እንደሆኑም ሀሳብ ሰጥተውበታል፡፡ ስልጠናውን ያዘጋጀው የተቋማችን ሰው ሀብት ልማት ዳይሬክቶሬት ነው፡፡
Recent Comments