ቱ. ማ. ኢ የካቲት 10/2015 ዓ ም በምስራቅ አፍሪካ ካሉ አገራት East Africa Skill for Transformation and Regional integration Project /EASTRIP/ ኢትዮጵያ፣ ኬንያ እና ታንዛኒያ የሚገኙበት ይህ የአምስት ዓመት ፕሮጀክት በቱሪዝም ዘርፉ የተቀላቀለው ተቋማችን የፕሮጀክቱ ተጠቃሚ ተቋማት ጋር እንዲሁም በሀገራችን የሀዋሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ስለ ስራው እንቅስቃሴና በሥራ ላይ ያሉ ተሞክሮዎችን ያካተተ የልምድ ልውውጥ ተካሄደ፡፡

በዓለም ባንክ የፕሮጀክቱ አስተበባሪዎች፣ የኬንያና የታንዛንያ ልዑካንን ተቀብለው ስለፕሮጀክቱ ገለፃ ያደረጉት የኢንስቲትዩቱ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ይታሰብ ስዩም ፕሮጀክቱ ተቋማችንን በአቅም ግንባታ ስልጠናና በመሰረተ ልማት ግንባታ በጣም ወሳኝ መሆኑን ጠቁመው በዚህ መስክ ተሞክሯችሁን ልታካፍሉን እዚህ ድረስ ስለመጣችሁ እናመሰግናለን ብለዋል፡፡ በፕሮጀክቱ ሊሰሩ የታቀዱ ሥራዎችን አስተባባሪው አቶ አብርሃም ለገሰ ገለፃ አድርገዋል፡፡
የሀዋሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የፕሮጀክት ስራዎችን ተሞክሮ ለመቅሰም የሄዱት የተቋሙ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ አባተና የፕሮጀክቱ ቴክኒካል ኮሚቴዎች እንደገለጹት ተቋሙ ለፕሮጀክቱ አዲስ በመሆኑ ቀድመው መሰራት ያለባቸውን ስራዎች፣ በሥራ ላይ ለሚያጋጥሙ ችግሮች የተሰጡ መፍትሔዎችን ከእናንተ ልምድ መቅሰም ስላስፈለገ ነው ብለዋል፡፡
አቶ መለሰ ዲዳሞ የሀዋሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የፕሮጀክት አስተባባሪ እንደገለጹት ፕሮጀክቱ እንደሀገር አዲስ እንደሆነና ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በዚህ ፕሮጀክት መግባቱ እድለኛ ተቋም መሆኑን ጠቁመዋል። ፕሮጀክቱን ለመሳካት በቡድን ልምድ ከመቅሰም መጀመራችሁ እኛን ያጋጠሙንን ችግሮች እንድታልፏቸው ይረዳችኋል ብለዋል።
ፕሮጀክቱን ስኬታማ ለማድረግ ለተቋሙን ማህበረሰብ እና ለባለድርሻ አካላት መረጃ መስጠትና ስለፕሮጀክቱ ሙሉ ግንዛቤ መስጠት እንደሚገባም አቶ መለሰ ተናግረዋል።
ስለ ፕሮጀክቱ እና አስፈላጊ የሆኑ ጉዳዮች ከኬንያና ታንዛንያ የመጡትም የሀዋሳ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎችም አጠቃላይ መረጃ እና ገንቢ አስተያየት ሰጥተዋል፡፡