ሆ.ቱ.ሥ.ማ.ኢ ነሐሴ 28/2011 ዓ.ም የኢፌዲሪ ባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ሆቴል እና መሰል አገልግሎት ሰጪ አሰሪዎች ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር የተዘጋጀው የአንደኛው የሀገር አቀፍ የሆቴል እና ቱሪዝም ኮንፍረንስ ዛሬ ሸራተን አዲስ ሲጀመር ተገኝተው መልዕክ ያስተላፉት የኢፌዲሪ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ክቡር አቶ ደመቆ መኮንን እንደገለፁት “መንግስት በጀመረው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ውስጥ የቱሪዝም ዘርፉ አንዱ ነው፡፡ በተለይም የቱሪዝም ዘርፍ የማክሮ ኢኮኖሚ መዛባት ችግሮችን ለመቅረፍ ትልቅ አቅም እንደሆነ መንግስታችን በፅኑ እንደሚምን ገልጸዋ፡፡
አያዘውም በቱሪዝም እሴት ሰንሰለት ውስጥ ያሉ ተዋናይ አካላትን አስተባብሮ የማስፈፀም አቅማቸውን ማጠናከር መሰረተ ልማቱን የማሻሻል የአገልግሎት አሰጣጡን ማዘመን እና በየደረጃው የተወዳዳሪነት ብቃትን ማጎልበት የሁሉም ሃላፊነት እንደሆነ ጠቁመዋው መንግስት በዘርፉ የሚታዩ ችግሮችን በተናጠል ለመፍታት የሚያደርገው ጥረት ረጅም ርቀት የሚያደርሰው ባለመሆኑ ከዘርፉ ባለሃብቶች ጋር ተቀራርቦ ለመስራት ከመቼውም ጊዜ በላይ ዝግጁ መሆኑን በመድረኩ ተናረዋል፡፡ በቀጣይም ሴክተሩንም ቁልፍ የእድገት መንገድ አድርጎ የወሰደው በመሆኑ ምቹ የስራ ሁኔታ የመፍተጠር የዘርፉን ጤንነት በትኩረት ለማስጠበቅ የተወዳዳሪነት አቅሙን የመገንባት እና በሌሎች መስኮች ሁሉ ድጋፉን አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡” ሲሉ ገልፀዋል፡፡
የኢፌዲሪ የባህልና ቱሪዝም ሚንስትር ክብርት ዶ/ር ሂሩት ካሳው በበኩላቸው እንደገለፁት “ኢትዮጵያ እንደ አፍሪካም ሆነ እንደ ዓለም በዘርፉ ያላት ድርሻ ሲፈተሸ ካላት እምቅ አቅም አንጻር ተጠቃሚ እዳትሆና ያደገጓት በረካታ ምክንያቶችን መጥቀስ ቢቻልም በዋናነት ተወዳዳሪ ሊያደርግ የሚችል ጥራት ያለው አገልግሎት አሰጣጥ ያለመቻሉ፣ የመስህብ ቦታዎች በተገቢው ሁኔታ ለምተውና ተወዳዳሪ ሆነው አለመገኘታቸው በዋናነት አንስተዋል፡፡
ይህን ችግር መለቅረፍ መንግስት ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ለዘርፉ ትኩረት በመስጠት ችግሩን ለማቃለልና ከዘርፉ የሚገኘውን ጥቅም ለማጎልበት ከባለድርሻ አካላትና ከህብረተሰብ ወኪሎች ጋር እየተመካከረና ተጨባጭ ሥራዎችን ለማከናወን እየተንቀሳቀሰ እንደሆነም ጠቅመዋል፡፡ አያይዘውም ሚኒስቴር መስሪያ ቤታቸው በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ ተሰማርተው ገንቢ እንቅስቃሴ ከሚያደርጉ አካላት ጋር ልዩ ልዩ ምክክሮችን ሲያደርግ እንደቆየና የጉባኤው መዘጋት በቱሪዝምና መስተንግዶ ኢንዱስትሪው መንግስትና የግሉ ዘርፍ በጋራ በመመካከር የወደፊት አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ በማሰብ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር የተዘጋጀ መድረክ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡
የኢትዮጵያ ሆቴል እና መሰል አገልፍሎት አሰሪዎች ፌዴሬሽንን በመወከል ንግግር ያደረጉት ፕሬዝዳንቱ አቶ ፍህ ወልደሰንበት በበኩላቸው “ሀገራችን ሀብት የሆኑ መስቦች በተገቢው እንዲጎበኙ እና የሀብት አመንጪ እንዲሆኑ በየመዳረሻዎቻችን ለቱሪስት የሚመጥን የመሰረተ ልማት ስራዎች ልንሰራ ሊሰራ እንደሚገባ ገልጸው ዋነኛው እና የቱሪስቱን የመቆየት ሁኔታ የሚወስነው እና ቱሪስቶች ብዙ እንዲያወጡ እና መስቦቻችን ሀብት አመንጪ እንዲሆኑ የሚያደርገው የሆቴል እና መሰል አገልግሎቶች ይጠይቃ ብለዋል፡፡
አክለውም ሀገራችን በአሁኑ ወቅት በኮንፍረንስ ቱሪዝም ላይ ያተኮረ የሚመስል ማስተዋወቅን እየተከተለች መገኘቷ የቱሪስት መስቦች ላይ የሚመጣው የቱሪስት ፍሰት እጅጉን አነስተኛ እንደሆነ ነው ጠቁመው የቱሪስት ፍሰትን ለመጨመር እና ቆይታውንም ለማርዘም መዳራሻዎቻችንን ማልማት እና ማስተዋወቅ ቀዳሚ ተግባራችን ማድረግ ይገባል፡፡” ሲሉ ገልፀዋል፡፡
በኮንፍረንሱ ላይ በሆቴል እና ቱሪዝም ዘርፍ የተሰማሩ ባለሀብቶች፤ ባለሙያዎች፤ ባለድርሻ አካላት፤ የተለያዩ ሚኒስትሮች፤ የክልል ርዕሰ ብሄራት እና ከንቲባዎች እንዲሁም ለሆቴል እና ቱሪዝም አቀራቢ ድርጅቶች እና አማካሪዎች ይሳተፋሉ፡፡ ኮንፈርነሱ በቀጣይም አህጉራዊ ይዘት ኖሮት እንደሚቀጥል በመድረኩ ላይ ተገልጿል፡፡
ምንጭ Ethiopian Tourism Culture
#በብሩክታደሰ
Recent Comments