ሆ.ቱ.ሥ.ማ.ማ ጥር 22 /2013 ዓ.ም የሆቴልና ቱሪዝም ማሰልጠኛ ማዕከል የ2013 በጀት ዓመት የስድስት ወር ዕቅድ አፈጻጸምና የሱፐርቪዥን ሪፖርት ለሰራተኞች ቀርቦ ውይይት አድርገውበታል።
በውይይቱ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ አስቴር ዳዊት መድረኩ ሰራተኞች የቀጣይ ስራዎች የሚለዩበትና የታዩ ክፍተቶችን ለማሻሻል ውይይት የሚደረግበት ነው ብለዋል።
የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም በእቅድ በጀትና ግምገማ ዳይሬክቶሬትና የሱፐርቪዥን ሪፖርት በለውጥና መልካም አስተዳደር ዳይሬክቶሬት የቀረበ ሲሆን ሰራተኞች በቀጣይ መስተካከል አለባቸው ያሏቸውን ሃሳቦችን አንስተው ውይይት ተደርጎበታል።
በቀረበው የሱፐርቪዥን ሪፖርት ላይ ከሰራተኞች የቀረቡ አስተያየቶችንና ቅሬታዎችን የተቋሙ የበላይ ኃላፊዎች ምላሽ የሰጡ ሲሆን በቀጣይ ስድስት ወር በአሰራር ምላሽ የሚያገኙ መሆናቸውን ጠቁመዋል።
ውይይቱ እስከ ነገ ይቀጥላል ተብሎ ይጠበቃል።
ትክክለኛ የሆቴልና ቱሪዝም ሥራ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ፌስቡክ ገጽን ላይክ በማድረግ ትክክለኛ መረጃ ያግኙ!