በቱሪዝምና ሆቴል ሙያ ሰልጥነው ከተመረቁ ተማሪዎች መካከል 87 በመቶ የሚሆኑት የሥራ እድል ተጠቃሚ ሆነዋል ተባለ።የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ኢስትሪፕ ፕሮጀክት ቴክኒካል አማካሪ ቦርድ አባላት የ2018 በጀት ዓመት የሩብ ዓመት አፈፃፀም በገመገሙበት ወቅት ነው ይህ የተገለጸው።የኢንስቲትዩቱ ተመራቂዎች ያሉበትን ሁኔታ የሚዳስስ ትሬሰር ጥናት የጥናትና ምርምር አስተባባሪ በአቶ አህደር ጠና ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።
በጥናቱ 87 በመቶ የሚሆኑት የኢንስቲትዩቱ ተመራቂዎች የሥራ እድል ተጠቃሚ መሆናቸው ተገልጿል።
የቴክኒካል አማካሪ ቦርዱን በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሶስት ወር አፈፃፀም መድረክን አስመልክቶ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር እንደገለጹት አማካሪ ቦርዱ በየትኛውም ተቋሙ በሚያቀርብለት ጥሪ በመገኘት ሙያዊ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን እና ኢንስቲትዩቱ ውጤታማ ለሆነባቸው የተለያዩ ክንውኖች ሁሉ ለነበራቸው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።
ከፕሮጀክቱ በተገኘ ድጋፍ በሪፎርም ሥራዎችና በISO21001:2018 ዓ.ምእውቅና ለማግኘት ጉልህ ሚና እንደነበረው ተገልጿል።
በውይይት መድረኩ የፕሮጀክቱ አስተባባሪ አቶ አብርሃም ለገሰ የሶስት ወር ክንውን ሪፖርት አቅርበዋል።
የውጭ ከታንዛንያ ናሽናል ቱሪዝም ኮሌጅ የተገኘ ተሞክሮ ቅመራ ሪፖርት በአቶ ይታሰብ ስዩም ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et


Recent Comments