ለውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት የአሰልጣኞች ስልጠና ተሰጠ

ቱ.ማ.ኢ
ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በሀገሪቱ ካሉት የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ለውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ለሚያሰለጥኑ አሰልጣኞች ስልጠና ሰጠ።
ስልጠናውን አስመልክቶ የእንኳን ደህና መጣች መልዕክት ያስተላለፉት በተቋማችን የEASTRIP አስተባባሪ አቶ አብርሃም ለገሠ እንደገለጹት ይህ ፕሮጀክት በሀገሪቱ በሆቴል ዘርፍ ያለውን የክህሎት ክፍተት በመሙላትና አንዱ ከሌላው ልምድ እንዲለዋወጥ የሚያስችል መሆኑን በመጠቆም በክልሎች ያሉ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ለውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ስልጠና የሚሰጡ ተቋማት ስልጠናዎች ተመሳሳይ እንዲሆኑ ማድረግና ብቁ የሰለጠነ የሰው ሀይል በመገንባት ለገበያ ለማቅረብ ማሰልጠኛው ከፕሮጀክቱ ጋር እንደሚሰራ ተናግረዋል።
ስልጠናው በሀገሪቱ ካሉት የቴክኒክና ሙያ ተቋማት 92ቱ ለውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ስልጠና ከሚሰጡት ለመጀመሪያ ዙር 61 እንዲተሳተፉ መደረጉን የተቋሙ ስልጠናና የተቋማት ግንባታ ዴስክ ኃላፊ አቶ ተመስገን በቀለ ገልጿል ።
በመቀጠልም ስልጠናው ዜጎች በያሉበት አገልግሎት እንዲያገኙና ወጥ የሆነ ደረጃ ኖሮት አሰልጣኞችን እንዲያሰለጥኑ ተፈልጎ ነው ብለዋል።
ስልጠናው በምግብ ዝግጅት እና ቤት አያያዝ ዙሪያ ሲሆን ለሦስት ቀን የሚቆይ ይሆናል።
ስልጠናው የሚሰጠው በተቋማችን አንጋፋ አሰልጣኞች ነው።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et/