“ቱሪዝም ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ” በሚል መሪ ቃል የጥናትና ምርምር ኮንፈረንስ እያካሄደ ነው።
====================
(ሚያዝያ 28/2013 ዓም) የሆቴልና ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከባህርዳር ዩንቨርሲቲ ጋር በመተባበር “ቱሪዝም ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት” በሚል መሪ ቃል የጥናትና ምርምር ኮንፈረንስ እያካሄደ ነው።
በፕሮግራሙ መክፈቻ ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ እና የሆቴልና ቱሪዝም ማሰልጠኛ ማዕከል ቦርድ ሰብሳቢ የቱሪዝም ዘርፉ ለዘላቂ ልማት ግብ ያለውን የጎላ ድርሻ አንስተዋል።
ፕ/ር አፈወርቅ አክለውም ቱሪዝም ከኢኮኖሚ ዘርፍ አንዱ በመሆኑ ከሆቴል ማህበራት፣ ከትምህርት ተቋማት፣ከማህበረሰብ አቀፍ ስራዎችና ታላቁ የህዳሴ ግድብን ጨምሮ የቱሪዝም ትስስር ማድረግ እንደሚገባ ገልፀዋል።
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትም ምርምር በማድረግ ዘርፉን ማገዝ እንደሚጠበቅባቸው አመላክተዋል ።
ዶ/ሂሩት ካሳው የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር በበኩላቸው በኢትዮጵያ ሰማይ ስር የቱሪዝም መስህብ የማይሆን ምንም ነገር የለም ። ከኛ የሚጠበቀው የዘርፉ ሙሁራንን በመጠቀም በጥናት የተደገፈ ሥራ በስፋት ማስተዋወቅ እና ማልማት ነው ብለዋል።