ቱማኢ ጥር/24/2018 ዓ ምቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ለአመራሮችና ሠራተኞች በሥራ ላይ ስነምግባር ዙሪያ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ።የተቋሙ ስነምግባር መከታተያ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ብርሃኑ ኩምሳ የሥራ ላይ ስነምግባር የተፈቀደ፣ የተወደደ፣ ያማረ ሥራ ወይም ድርጊት ማለት መሆኑን እና የሥራ ላይ ስነምግባር
ማለት በሥራ ሰዓት መገኘት፣ መከባበር ፣እምነት የሚጣልበት ሰው መሆን፣ የሥራ ተነሳሽነት እንዲኖር የሚሉ ሀሳቦችን ተነስተዋል።በመቀጠልም የተቋሙ ተቋማዊ ለውጥ ሥራ አስፈፃሚ አቶ ተፈራ በዳዳ በተቋሙ በ2016 ዓ ም እና በ2017 ዓ ም ለሠራተኛው የተሰጠው የተለያየ ርዕስ ያለው ስልጠና ያመጣውን ውጤት የሚዳስስ የጥናት ሰነድ አቅርበዋል። በጥናቱ የቸሰጡ ስልጠናዎች 85 በመቶ ውጤታማ መሆናቸው ተገልጿል።
ሌላው በ2018 ዓ.ም በተቋሙ ማማከር ዘርፍ የተሰሩ በአዲስ አበባ 63 ሆቴሎች፣ በባሌ 25፣ በሸገር ከተማ በ42 በተመረጡ ሆቴሎችና ሪዞርቶች እና 10 ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጆች ማማከር እንደተሰጠ የተቋሙ የማማከርና ማርኬቲንግ ዴስክ ኃላፊ አቶ ታምራት ተፈራ ገልጸዋል።
በመጨረሻም በዶ/ር አስቻለው አዳራ እየተሰራ ባለው ተቋማዊ ግምገማ( self evaluation document) የደረሰበትን ደረጃ ለሠራተኛው አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል።
ለቀረበው ጥያቄና አስተያየት በተቋሙ ምክትል ዋና ዳይሬክተሮች ምላሽ ተሰጥቶበታል።
ትክክለኛ መረጃ ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et


Recent Comments