ቱ ማ ኢ ታህሳስ 24/2018 ዓ.ም ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት አዲስ ለገቡ መደበኛ ሰልጣኞች የኤች አይቪ ኤድስ መከላከል እና የስነ ተዋልዶ ጤና አጠባበቅ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ከጤና ሚኒስቴር ኤች አይቪ ኤድስ መከላከል ክፍል በመጡ ባለሙያ ወ/ሪት ህይወት ሽብሩ ተሰጥቷል፡፡በስልጠናው ለተገኙ ሰልጣኞች እድሜያቸውን መሰረት ያደረገ የኤች አይቪ ኤድስ ተጋላጨነትን መከላከል የሚያስችል ሰነድ ወ/ሪት ህይወት ያቀረቡ ሲሆን በ2024/2025 በተደረገ ጥናት እድሜያቸው ከ15 እስከ 24 የእድሜ ክልል ያሉ ወጣቶች ከፍተኛውን ቁጥር (34% )የሚይዙ መሆኑን ከፆታ አኳያ ሴቶች ተጋላጭ እንደሆኑ ፣ ከከተሞች አኳያ አዲስ አበባ ከፍተኛ የስርጭት ምጣኔ ያለበት እንደሆነ ጠቅሰዋል፡፡

ስለሆነም ሰልጣኞች ራሳቸውን መከላከል ያለባቸው መሆኑን በመረጃ በተደገፉ ጥናቶች አቅርበዋል።
በአሁኑ ጊዜ ስለ ኤች አይቪ አይወራም ማለት ስርጭቱ የለም ማለት እንዳልሆነ ተገንዝበው ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ወ/ሪት ህይወት አሳስበዋል፡፡
በጨማሪም ስለ ስርዓተ ፆታ እኩልነት ፣ የስልጣኞች የስነምግባር እና ቅሬታ አፈታት ጉዳዮች ዙሪያ በስልጠና አስተባባሪዎቹ የሥርዓተ ፆታ ፣ ማህበራዊ ጉዳዮች ትግበራ እና የስነምግባርና ሙስና መከላከል ሥራ አስፈፃሚዎች ቀርቧል፡፡
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et