ታህሳስ 17/2018 ዓ ም
ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የላቀ ደንበኞች አገልግሎት አሰጣጥ ከተቋም ባለፈ ለመስራት ቀድሞ የተቋሙ ባለሙያዎችና ሠራተኞች ግንባር ቀደም ሆኖ እንዲገኙ ሁለተኛው ዙር ስልጠናዎችን እየሰጠ ይገኛል።
ለባለሙያዎች እና ሰራተኞች በሚሰጠው ስልጠና የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የተቋሙ ስልጠና እና አቅም ግንባታ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ክብረት ተቋማችን እንደሀገር በስልጠና በምርምርና ማማከር ዘርፍ በISO 21001:2018 እና በሪፎርም ግንባር ቀደም እንደሆነው ሁሉ በያዝነው በጀት ዓመት በላቀ ደንበኞች አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ልቀን ለመገኘት እየተሰራ በመሆኑም የተቋሙ ባለሙያዎችና ሰራተኞች ይህንን ስልጠና እንዲያገኙ እየተደረገ መሆኑን ገልፀዋል።

የተቋሙ ምርምርና ማማከር ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ይታሰብ ስዩም ባስተላለፉት መልዕክት የደንበኞች አገልግሎት አሰጣጥ የመልካም አስተዳደር ችግር የሚያመጣ በመሆኑ እኛ ሞዴል ሆነን በሂደት የሆስፒታሊቲ ዘርፍ ከፍ አድርገን መስራት እንደምንፈልግ በመጠቆም የላቀ የአገልግሎት አሰጣጥ በይዘቱ ጥልቅ በመሆኑ ትኩረት ሰጥተው መሰልጠን እንዳለባቸው ተናግረዋል።
የዛሬን ስልጠና የሰጡት አሰልጣኝ አቶ ዳንኤል በቀለ የላቀ የደንበኞች አገልግሎት ለማምጣት ደንበኞችን መለየት ዋና ተግባር በመሆኑ ግንዛቤ ሰጥተው ሁሉም አባላት በቡድን ተወያይተው ተገልጋዩን እንዲለዩ አድርጓል።
ሌላኛው አሰልጣኝ አቶ መለሰ ወርቁ የላቀ የደንበኞች አገልግሎት ለማምጣት ተቋማዊ ተግባቦት ላይ ትኩረት ተሰጥቶ መስራት እንዳለበት ገልፀዋል።
ስልጠናው በዚህ መልኩ ለቀጣይ ሦስት ቀን በተለያዩ አሰልጣኞች የሚቀጥል ይሆናል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et/