ቱ.ማ.ኢ ሰኔ 02/2017 ዓ.ም በስልጠና ፣ጥናትና ምርምር እና ማማከር አገልግሎት ረጀም ዓመታትን የሀገራችን ቱሪዝም እድገት እየደገፈ የሚገኘው ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ ከመጡ የሥራ ሃላፊዎች ጋር በተለይ በዘርፉ ያለውን የትምህርትና ስልጠና በቅንጅት መስራት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡በሀገራችን በሆቴልና ቱሪዝም ሙያዎች በከፍተኛ ትምህርት ደረጃ በሁለተኛና ሶስተኛ ዲግሪ ትምህርትና ስልጠና እየሰጡ የሚገኙ ከፍተኛ| የትምህርት ተቋማት እና በዘርፉ የሚገኙ ሙያተኞች ቁጥርም በቂ ባለመሆኑ ይህን ክፍተት ለመሙላት በሁለቱ ተቋማት በቅንጅት መስራት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከኢንስቲትዩቱ የሥራ ኃላፊዎች ጋር መክረዋል፡፡

ሁለቱ ተቋማት ከዚህ በፊት በተለያዩ መስኮች አብሮ ለመሥራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት አድርገው እንደነበርም በዚያም በጋራ የተሰሩ ሥራዎች በውይይቱ ተነስቷል፡፡
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et