በሥራና ክህሎት ዘርፍ የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርምን በተዋረድ ባሉ መዋቅሮች ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ ለማድረግ ያለመ የምክክር እና የአቅም ግንባታ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።
በመድረኩ የክልል ምክትል ቢሮ ኃላፊዎች ጨምሮ የሪፎርም አስተግባሪ ኮሚቴ አባላት በመሳተፍ ላይ ናቸው፡፡የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር እና የሚኒስቴሩ የሪፎርም ትግበራ አስተባባሪ አቶ ጌታቸው ነጋሽ ባስተላለፉት መልዕክት፤ በበጀት ዓመቱ ሪፎርሙን ሙሉ ለሙሉ ወደ ትግበራ ለማስገባት በትኩረት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡

በመጀመሪያ ዙር በሙከራ ትግበራ ደረጃ ከተመረጡ ስምንት ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች መካከል የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በዝግጅት ምዕራፍ የተሰጡትን ተግባራት በከፍተኛ ውጤታማነት ማከናወኑ ተጠቁሟል።
ሚኒስቴሩ በሪፎርም ትግበራው ውጤታማ እንዲሆን በዘርፉ ተግባራዊ ማድረግ የጀመራቸው ኣዳዲስ እሳቤዎችን ጉልህ ፋይዳ እንደነበራቸው አስታውሰዋል፡፡
የሪፎርሙ መነሻ የሲቪል ሰርቪሱ ዘርፉ ያለበት ነባራዊ ሁኔታ መሆኑን የጠቆሙት ዋና ዳይሬክተሩ ይህ ሪፎርም በዘርፉ የሚታዩ ክፍተቶችን ለመሙላት ወሳኝ ነው ሚና እንደሚጫወትም ተናግረዋል፡፡
የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም የበቃ የሰውኃይል ፣ ብቁና አስተማማኝ የሥራ ዕድል ለዜጎች የሞላባት ሀገር ለመፍጠር ሚኒስቴር መ/ቤቱ የያዘውን ራዕይ ለማሳካት የሚያስችል መልካም አጋጣሚ በመሆኑ ለትግበራው በቂ ዝግጅት ማደረግ ወሳኝ መሆኑ በአፅንኦት ተነስቷል፡፡
ጥር 20/2018 ዓ.ም፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
Official Website: mols.gov.et
Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE
Telegram: https://t.me/FDRE_MoLSofficial
TikTok: tiktok.com/@mols_official
Twitter / X: twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር
WhatsApp: whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtT