በውይይቱ የኢትዮጵያ ሆቴልና ቱሪዝም አሰሪዎች ፌደሬሽን፣ የኢትዮጵያ ቱር ኦፐሬተርስ ማህበር፣ የአዲስ አበባ ሆቴል ባለንብረቶች ማህበር እና የታልቅ ኢትዮጵያ አስጎብኝዎች ማህበር ፕሬዝዳንቶች የተገኙ ሲሆን በመስኩ በትብብር መስራት የሚያስችሉንን ጉዳች ተመልክተናል፡፡
በዘርፉ ያለውን የሰለጠነ የሰው ሃይል አቅርቦትን ለማሻሸል፣ የመንግስትና የግሉን ዘርፍ ትብብርና ቅንጅት ለማጠናከር እና እሴት ሰንሰለቱን መሰረት በማድረግ ጥራት ያለው የሥራ ዕድል መፍጠር የሚቻልበትን ሁኔታም በዝርዝር ተመልክተናል፡፡
መንግስት ለዘርፉ ልዩ ትኩረት በመስጠት ለኢኮኖሚው የሚያበረክተውን አስተዋጽኦ ለማሳደግ፣ ለሥራ ዕድል ፈጠራ ያለውን አቅም አሟጦ ለመጠቀና አጠቃላይ ስነ-ምህዳሩን ምቹ ለማድረግ ካለው ውስን ሀብት ወሳኝ የሆኑ መሰረተ ልማቶቹ እንዲሟሉ እያደረገ ይገኛ፡፡
ለዘርፉ የሰለጠነ የሰው ሃይል ፍላጎትም ምላሽ ለመስጠት በትኩረት እየሰራ ይገኛል፤ ይህንንም አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡ በዘርፉ ያሉ ተግዳሮቶችን ወደ ዕድል በመቀየር በዘርፉ ያሉ ማህበራት ሚና ከፍተኛ ነው፡፡
ዶ/ር ፍትህ ወልደሰንበት የኢትዮጵያ ሆቴልና ቱሪዝም አሰሪዎች ፌደሬሽን ፕሬዝዳንት፣ ወ/ሮ አስቴር ሰለሞን የአዲስ አበባ ሆቴል ባለንብረቶች ማህበር ፕሬዝዳንት፣ አቶ ፍጹም ገዛኽኝ የኢትዮጵያ ቱር ኦፐሬተርስ ማህበር ፕሬዝዳንት እና አቶ ዳንኤል ተስፋየ የታልቅ ኢትዮጵያ አስጎብኝዎች ማህበት ፕሬዝዳንት በትብብር ለመስራት ላሳያችሁን ቁርጠኝነት ከልብ የመነጨ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ፡፡
የሥራ ባለቤት እርስዎ ነዎት!

Recent Comments