ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በፌዴራል ደረጃ ያዘጋጀው ቱሪዝምና ዲጅታላይዜሽን የሚል ጥናት በአማራ ክልል ደሴ ከተማ ቀረበ። ጥናቱን ያቀረቡት የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የቴክኖሎጂ ሽግግር ዲን አቶ ዳዊት ኃ/ሚካኤል ሲሆኑ

በጥናቱ የተለዩት ቴክኖሎጂዎች አፕልኬሽን ከመስራት እስከ ቁሳዊ እቃዎች ምርት የተጠኑ ሲሆን ሀገራችን ከሏት እንደ ህዳሴ ግድብ እና ጣና ሀይቆች ላይ ተጨማሪ መስህብ እንዲሆኑ የውሃ ላይ ሆቴሎች (floating hotel)፣ አንድ ጎብኝ ከአካባቢው ማህረሰብ ጋር ለመግባባት እንዲችል የቋንቋ መተርጎሚያ አፕልኬሽን፣ ጎብኝ ፓርክ ውስጥ ሲገባ መንገድ እንዳይጠፋው የሚረዳ ጂፒኤስ እና በተለይ ከውጭ የሚገቡ ጉብኝዎች የሚጠቀሙበት ታጣፊ ወንበሮች ምርቱን በሀገር ውስጥ መስራት እንደሚቻል ገልጸዋል፡፡
አቶ ዳዊት እንደገለጹት እነዚህን እና መሰል የዲጂታል መሳሪያዎች መጠቀም ዘመኑ የሚጠይቀው መሆኑን ነው፡፡
ጥናቱ የአማራ ክልል ቱሪዝም ቀን በሚከበርበት ወቅት የቀረበ ሲሆን የክልልሉና የደሴ ከተማ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et