ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩቱ በ2017 ባከናወናቸው ጥናትና ምርምሮች ላይ ውይይት ተካሄደ ።ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በበጀት ዓመቱ በቱሪዝም እሴት ሰንሰለት፣ የሆስፕታሊቲ ዘርፉ አስፈላጊ ቴክኖሎጂዎች፣ የባህል ምግቦች ዝግጅት ሀገር በቀል እውቀቶችና ሌሎችም ርዕሶች ላይ ባካሄደው ችግር ፈቺ ጥናትና ምርምሮች ላይ ውይይት ተካሄደ ።በጥናት ጉባኤው ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ በበጀት ዓመቱ በተቋሙ የተሰሩ ጥናቶች እንደ ሀገር ለዘርፉ እድገት የሚያግዙ ናቸው ብለዋል።
ኢንስቲትዩቱ የራሱን ባለሙያዎቾ በመጠቀም በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ እያካሄደ የሚገኘው ጥናት እያደገ መምጣቱን የገለጹት አቶ ጌታቸው ነጋሽ እንዲህ አይነቱ የምርምር ውጤትን መነሻ በማድረግ ሌሎች ሴክተር መስሪያ ቤቶች እንደ ግብዓት እየተጠቀሙበት ይገኛሉ ብለዋል።
የጥናትና ምርምር ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ይታሰብ ሥዩም በበኩላቸው የተሰሩ ጥናቶች በዘርፉ እድገት ላይ የወደፊት አቅጣጫዎችን የሚያመላክት እንደሆነ ገልጸዋል ።
በ2017 ዓ.ም በቱሪዝም እሴት ሰንሰለት፣ በዘርፉ ቴክኖሎጂዎች ሽግግር ፣ በሆቴልና ቱሪዝም ሙያዎች የደረጃ ስድስት እና ሰባት ስልጠና ፍላጎት እና የባህል ምግቦች ለቱሪዝም ዘርፉ እድገት ያለው አስተዋጽኦ ላይ ያተኮሩ ጥናቶች መሰራታቸውን አቶ ይታሰብ ገልጸዋል።
የሆቴልና ቱሪዝም ሙያዎች ስልጠና በደረጃ VI እና VII ያለውን ፍላጎት ጥናት ያቀረቡት አቶ ሳህሌ ተክሌ ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለ ጥናቱ እንደሚያመለክት ገልጸዋል ።
በመርሐ ግብሩ ላይ ሰባት የጥናት ውጤቶች ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል ።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et


Recent Comments