የኢንስቲትዩቱ አመራርና ሠራተኞች ብሔራዊ ጥቅምና ጂኦስትራቴጂያዊ ቁመና በሚል ርዕስ በተዘጋጀ ሰነድ ዙሪያ ስልጠናዊ ውይይት አካሄዱ። ጥቅምት 7/2018 ዓ.ም ቱ.ማ.ኢ

ስልጠናውን የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ ጌታቸው ነጋሽ የከፈቱ ሲሆን በመልእክታቸውም ወቅታዊና ሀገራዊ በሆኑ ጉዳዮች ዙሪያ ሠራተኛው ግንዛቤ እንዲኖረውና የበኩሉን ኃላፊነት ለመወጣት እንዲችል መድረኩ መዘጋጀቱን ተናግረዋል።አቶ ጌታቸው አክለውም ሠራተኛው በብሔራዊ ጥቅም ጉዳይ ላይ ውስጣዊ አንድነታችንን በማጠናከር በጋራ መቆም እንዳለበት መልእክት አስተላልፈዋል።
የስልጠና ሰነዱን የኢንስቲትዩቱ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ይታሰብ ስዩም ያቀረቡ ሲሆን በሰነዱ በጉልህ ከተነሱ ነጥቦች ውስጥ የኢትዮጵያ ጂኦስትራቴጂያዊ ቁመናና ብሔራዊ ጥቅም፣ የብሔራዊ ጥቅም ዋነኛ ፈተናዎች፣ ለብሔራዊ ጥቅም መረጋገጥ ቁልፍ መፍትሔዎች፣ ለብሔራዊ ጥቅሞቻችን መረጋገጥ የሚጠበቅብን ሚና እና የተቋማት ጂኦስትራቴጂያዊ ቁመና በተቋም ውጤታማነት ላይ እንዴት ተፅዕኖ እንደሚያሳርፍ በዋነኝነት ይጠቀሳሉ።
በመድረኩ በርካታ አገራዊ እና ወቅታዊ ጉዳዮች የተነሱ ሲሆን በተለይ ከታላቁ ህዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ የተሻገርነውን የአሸናፊነት ድል እና ከታሪካዊ ወደቦቻችን በተያያዘ ዓለም አጀንዳው እንዲያደርገው መደረጉ፣ ሠራተኛው በአገልጋይነት መንፈስ ሥራውን መስራት እንደሚጠበቅበት በተሳታፊዎች በኩል ተነስቶ ጥልቅ ውይይት ተደርጎበታል።
በተጨማሪም ኢትዮጵያን ወደ ቀደመ ክብሯ ለመመለስ የሀገርን ገጽታ የሚገነቡ በርካታ ትልልቅ ሥራዎች እየተሰሩ ህዝቦች ከተረጅነት ራስን ወደ መቻል፣ የነዳጅ እና የማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ እና ሌሎች አንኳር ፕሮጀክቶች ሥራላይ መሆናቸው ተገልጿል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et