የ2018 በጀት ዓመት እቅድና የአንደኛ ሩብ ዓመት አፈፃጸም ሪፖርት ለሰራተኞች ቀረበ።

የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት 2018 በጀት ዓመት እቅድና የአንደኛ ሩብ ዓመት አፈፃፀም ሪፖርት እና የኢንስቲትዩቲ የአስር ዓመት ፍኖተ ካርታ ለሰራተኞች ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።
ለሠራተኞች የቀረበውን ሪፖርትና የአሥር ዓመት ፎኖተ ካርታን አስመልክቶ የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ እንደተናገሩት በ2018 በጀት ዓመት ሊሰሩ ከታቀዱት መሀከል በአንደኛ ሩብ ዓመት የተሰሩ ሥራዎች በርካታ መሆናቸውን እና ለዚህ ሥራ ሁሉም የድርሻውን መወጣቱ ገልጸዋል።
በበጀት ዓመቱ በዋናነት የISO ሰርትፊኬሽን፣ የዓለም ቱሪዝም ቀን አከባበር ፣ ከኩሪፍቱ አፍሪካ ቨሌጅ ጋር በመተባበር የተዘጋጀው ባህላዊ የምግብ ፌስቲቫል በቀዳሚነት የሚነሱ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።
ፍኖተ ካርታው ሀገራዊ ሰነድ የሚሆን እንደሆነና ግብዓት የሚሆኑ ሀሳቦችን እየወሰድን የምናሳድገው እንደሆነ ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።
የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በ2018 በጀት ዓመት ለመስራት የታቀዱ ሥራዎችና በዚሁ ዓመት በ1ኛ ሩብ ዓመት የተሰሩ ሥራዎችን በተመለከተ የተቋሙ ስትራቴጂክ ጉዳዮች ሥራ አስፈጻሚ አቶ ዳግም አዲሱ አቅርበዋል።
ዋና ዋና ግቦች የአገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም፣ የሥልጠና አግባብነትና ጥራት ማሻሻል፣ የስልጠና ፍትሐዊ ተደራሽነትን ማሳደግ፣ የምርምርና ማማከርና ቴክኖሎጂ ሽግግርን ማሳደግ እና የድጋፍና ክትትል ሥራዎች በትኩረት የተሰሩ መሆናቸውንም አቅርቧል።
በዚህ ሩብ ዓመት በጥንካሬ ከተወሰዱ ጉልህ አፈፃፀሞች ISO21001:2018 ወደ ትግበራ መገባቱ ፣በየክልሎች የተሰራው ባህላዊ ምግብ በሆቴሎች ምግብ ዝርዝር እንዲገባ መሰራቱ ሲሆን እንደ ከፍተት በአንዳንድ ክፍሎች የባለሙያ እጥረት መታየቱ ተጠቅሷል።
ለቀጣይ ትኩረት አቅጣጫዎችም የሪፎርም ሥራ ማጠናከር ፣ የሚመለከታቸው አካላት ጋር ያሉ ግንኙነት ማጠናከርን ዲጅታላይዜሽን እና የሠራተኛ ስምሪት ትኩረት እንደሚያስፈልጋቸው ተገልጿል።
የተቋሙ የአሥር ዓመት ፍኖተ ካርታ በዶ/ር አስቻለው አደራ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል ።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.e