ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር የሥራና ክህሎት ሚኒስቴርና የተጠሪ ተቋማቱ አመራርና ሠራተኞች የሀገራዊ ለውጡን 7ኛ ዓመት በማስመልከት “ትናንት፣ ዛሬና ነገ ለኢትዮጵያ ልዕልና” በሚል መሪ ሃሳብ የፓናል ውይይት አካሂደዋል።

የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በመድረኩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ‹‹ትናንት፣ ዛሬና ነገን ለኢትዮጵያ ልዕልና !›› በሚል መሪ ሃሳብ የሚከበረው የለውጡ ሰባተኛ ዓመት ከትናንት የምንማርበት፣ ስለዛሬ አብዝተን የምንመክርበትና ለነገ መሰረት የምንጥለበት ነው ብለዋል፡፡
የለውጡ ጉዞ ትልልቅ ጉዳዮችን ከመሰረቱ ለመለወጥ የሚያስችሉ ተግባራት በተጨባጭ የተከናወነበት መሆኑን የገለፁት ክብርት ሚኒስትር ያልተሞከረ ነገር ግን ለኢትዮጵያ ቀጣይትና ዘላቂነት ግድ የሚሉ ጉዳዮች የተሞከሩበትና አዳዲስና ተጨባጭ ውጤቶችን የተመዘገቡበት መሆኑንም አስረድተዋል፡፡
ሀገራዊ ለውጡ እውን በሆነባቸው ዓመታት ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ስብራቶችን ለማከምና ለማዳን የሚያስችሉ ሰፋፊ ትልሞች የተቀረፁባቸው ከመሆኑም በላይ ቀን ከሌሊት በመትጋት ትውልድንና ሀገርን የሚያሻግሩ ውጤቶች ዕውን የሆኑባቸው ጊዚያት እንደነበሩም ክብርት ሚኒስትር አብራርተዋል፡፡
ከራስ በላይ ሀገር ማስቀደምና ፀንቶ መቆም የለውጡ ምሰሶዎች ናቸው ያሉት ክብርት ሚኒስትር ኢትዮጵያውያን ከጋራ ማንነታቸው በላይ በሰውነታቸው ክብር እንዲያገኙ ማስቻል ደግሞ ዋንኛ መዳረሻ ግብ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡
ባለፉት ሰባት ዓመታት የተሠሩ ሥራዎች ኢትዮጵያን ለትውልድ የምትበቃ ሀገር እንድትሆን ማድረግ የሚያስችል ነባራዊ ሁኔታን የፈጠሩ መሆናቸውን በአፅንኦት በማንሳትም የማይቋረጠው የህዳሴ ጉዞ የኢትዮጵያ ልዕልና እስከሚረጋገጥ ድረስ በፅናት ይቀጥላል ብለዋል፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ተሻለ በሬቻ(ዶ/ር) በበኩላቸው ለውጡን ተከትሎ የትምህርትና ስልጠና ስርዓት መቀየሩ በዘርፉ የማደግና የመለወጥ ህልምን እውን ያደረገ ነው ብለዋል።
የቴክኒክና የስልጠና ተቋማት ከደረጃ አምስት ወደ ደረጃ ስምንት አድጎ መምጣቱ በዘርፉ እውቀቱን ለማዳበር ፍላጎት ያለው ሰው በሙያው በፒኤች ዲ ትይዩ የሆነ የትምህርትና ስልጠና እድል እንደተመቻቸ የገለጹት ተሻለ በሬቻ(ዶ/ር) ከለውጡ ትሩፋቶች የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ፖሊሲና የህግ ማዕቀፍ መዘጋጀቱ ዘርፉ ሥራ ፈጣሪ እንዲሆን እድል እንዲያገኝ አድርጓል ብለዋል ።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et