ቱ.ማ.ኢ ነሐሴ 08/2017 ዓ.ም የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ሠራተኞችና የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር ቱሪዝም ኮሚሽን ጽ/ቤት ጋር በመሆን በከተማዋ አቅራቢያ በሚገኘው አረንጓዴ ሀይቅ አካባቢ ችግኝ ተክለዋል።

በመርሐ ግብሩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ ተቋሙ ከኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽን ጋር በስልጠና፣ በጥናትና ምርምር እንዲሁም የማማከር አገልግሎት ለመስጠት እና ዘርፉን ለማጠናከር ስምምነት በተደረገው መሰረት አብሮ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
አካባቢው ለጎብኝዎች ምቹ እንዲሆን ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩቱ በሚሰራቸው ሥራዎች አስፈላጊውን ሁሉ ትብብር እንደሚያደርግ አቶ ጌታቸው ነጋሽ ጨምረው ተናግረዋል።
የኢንስቲትዩቱ የጥናት ምርምርና ማማከር ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ይታሰብ ሥዩም በበኩላቸው ለችግኝ ተከላ መርሐግብር የተመረጠው ቦታ ለኢኮ ቱሪዝም እና የማህበረሰብ አቀፍ ቱሪዝምን ለማሳደግ ትልቅ አቅም ስለሚሆን ከአዲስ አበባና ቢሾፍቱ ከተማ ካለው ቅርበት የጎብኚዎች መዳረሻ እንዲሆን መሰራት ይገባል ብለዋል።
የከተማ አስተዳደሩ ቱሪዝም ኮሚሽን ጽ/ቤት የቱሪዝም ልማት ቡድን መሪ አቶ አንተነህ እሼቴ በበኩላቸው አካባቢው እንዲተዋወቅና መዳረሻ እንዲሆን ከኢንስቲትዩቱ ጋር እንደሚሰራ ገልጸዋል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et