የተከበሩ ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ የሰው ሀብት ልማት፣ሥራ ሥምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 23ኛ መደበኛ ስብሰባው የሥራና ክህሎትሚኒስቴርን የ2017 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ተመልክቷል፡፡የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ሪፖርቱን ያቀረቡ ሲሆን የምክር ቤት አባላቱ ላነሷቸው ጥያቄዎችም ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
በዚህም ባለፉፍት ዘጠኝ ወራት የቴክኒክና ሙያ ተቋማትን የኩባንያዎች መፈልፈያ እንዲሆኑ ታሳቢ በማድረግ በተከናወኑ ሥራዎች ተጨባጭ ውጤቶች የተመዘገቡ መሆኑን የጠቆሙት ክብርት ሚኒስትር ተቋማቱ ከሥልጠና ባሻገር ባለው ተልዕኳቸው የሥልጠና ጥራታቸውን ማረጋገጥ የሚያስችላቸውን ሥራ በመስራት በቢሊየን የሚቆጠር አዲስ ሀብት መፍጠር ጀምረዋል ብለዋል፡፡
በሥራ ዕድል ፈጠራ ዘርፉም በሀገር ውስጥ፣ በውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት እና በርቀት ሥራ 3.4 ሚሊዮን የሚሆኑ ዜጎችን ጥራት ያለው የሥራ ዕድል ተጠቃሚ ማድረግ እንደተቻለም አመላክተዋል፡፡
የሰው ሀብት ልማት፣ሥራ ሥምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ በበኩላቸው በሥራ ዕድል ፈጠራው የተከናወኑ ሥራዎች አበረታች መሆናቸውን ገልፀው ያለው ፍላጎት ከፍተኛ በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አመላክተዋል፡፡
ሚኒስቴሩ የመንግስት የአገልግሎት ማሻሻያ ሪፎርም የመጀመሪያ ምዕራፉን አጠናቆ ለቀጣዩ ምዕራፍ እየተዘጋጀ መሆኑ የሚያበረታታ መሆኑን ገልፀው በቀጣይም ለሌሎች ሞዴል በሚሆን መልኩ ትግበራውን አጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል፡፡
የሥልጠና ተቋማትን የኩባንያዎች መፈልፈያ እንዲሆኑ ለማድረግ የተጀመረው ሥራ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ያሉት የተከበሩ ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ የሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች ጋር በተያያዘ እያጋጠመ ያለውን ችግር ለመቅረፍ ጥብቅ ክትትል እና ቁጥጥር እንዲደረግ አሳስበዋል፡፡
ሚያዝያ 2፤ 2017
ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መረጃ በሚከተሉት የማህበራዊ ትስስር ገፆች ይከታተሉን፡
በድረገጽ፡- http://mols.gov.et/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MolsFDRE
ቴሌግራም፦ https://t.me/fdre_mols
ዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtTbPZtDW1y
ቲክቶክ:- tiktok.com/@mols_official
ሊንክዲን፡- https://www.linkedin.com/…/ministry-of-labor-skill-fdre/!

Recent Comments