ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ጋር በመተባበር በደሴና አካባቢው የሚገኙ ባህላዊ ምግቦች እና መጠጦችን የጥናቱ አካል አድርጓል፡፡
የባህላዊ ምግቦች እና መጠጦቹ በኢንስቲትዩቱ ሼፍ ብሩክ አዳሙ እና

በሌሎች የተቋሙ ባለሙያዎች እና በአከባቢው ከሚገኙ እናቶች ጋር በትብብር በሆቴሎች የምግብ ዝርዝር ወስጥ እንዲካተቱ ለማድረግ በከፊል ከተጠኑት ምግቦች መሃል ቃተኛ፣ አነባብሮ ፣ ጭብጦ፣ ሪጦ፣ ተልባ ወጥ፣ ድርሚሶ፣ ስልጆ፣ ሽንብራ አሳ፣ ሳማ ወጥ እና ከመጠጦች አረቄ፣ ኮረፌ፣ ጠጅ እና ቡቅሬ ቀርቦ በክልሉ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም በሀገር ሽማግሌዎች ቅምሻ ተደርጓል።
የአማራ ክልል ባህል ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ መልካሙ ፀጋዬ ኢንስቲትዩቱ ባህላችንን ለማስተዋወቅ ላደረገው አስተዋጽኦ እናመሰግናለን ብለዋል፡፡
ኢንስቲትዩቱ እስካሁን ከ200 በላይ ባህላዊ ምግቦችና ከ15 በላይ ባህላዊ መጠጦችን ማጥናትና መሰነዱ ይታወሳል፡፡
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et