ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከኩሪፍቱ አፍሪካ ቪሌጅ ጋር በመተባበር የኢትዮጵያ ባህላዊ ምግቦች ፌስቲቫል አዘጋጅቷል።
ቱ.ማ.ኢ ጥቅምት 1/2018 ዓ.ም በዝግጅቱ ላይ በክብር እንግድነት ተገኝተው ፕሮግራሙን የከፈቱት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል እንደገለጹት ይህ የባህላዊ ምግብ ፌስቲቫል ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያ ከነሙሉ ክብሯ የተገለጸችበት ነው በማለት ገልጸውታል።
ይህን መሰል መድረክ መዘጋጀቱ ከጓዳ ያልወጡ አቅሞችን ወደ አደባባይ እንዲወጡ፣ የኢትዮጵያን ገጽታ እንዲያስተዋውቁ እና ለዜጎች በተለይም ለሴቶች የሥራ እድል የሚፈጥር በመሆኑ በመሆኑ ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚገባ ገልጸዋል።
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ በበኩላቸው ኢንስቲትዩቱ የኢትዮጵያ ባህላዊ ምግብና መጠጦችን ለዓለም አቀፍ ማህበረሰብ እንዲተዋወቁ የጥናትና ምርምር እንዲሁም ሙያዊ የማማከር ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።
በዚህም በጥናት የተለዩ የኢትዮጵያውያን ባህላዊ ምግብና መጠጦች በኩሪፍቱ አፍሪካ ቪሌጅ መቅረባቸውን ገልጸዋል።
የኩሪፍቱ ሪዞርቶች ባለቤት አቶ ታድዮስ ጌታቸው የኩሪፍቱ አፍሪካ መንደር የኢትዮጵያ ባህላዊ ምግቦችን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እያስተዋወቀ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።
በፌስቲቫሉ ላይ ከሁሉም ክልሎች የተመረጡ የብሔር ብሔረሰቦች ባህላዊ ምግቦች ቀርበዋል።
ፌስቲቫሉ በጥናት የተለዩ ባህላዊ ምግቦችን በማስተዋወቅ ወደ ገበታ እንዲመጡ ማድረግ፣ የእርስ በርስ ትውውቅን መፍጠር፣ የሀገር ገጽታ መገንባት እና የምግብ ቱሪዝምን ማሳደግ ያለመ መሆኑም ተገልጿል።
በዝግጅቱ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች፣ የውጪ ሀገር አምባሳደሮች፣ ባለ ድርሻ አካላትና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et

Recent Comments