ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በቱሪዝምና ሆቴል ዘርፍ ለሰልጣኞች የትብብር ስልጠና ለሚሰጡ ባለድርሻ አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ።
በመክፈቻ ፕሮግራሙ ንግግር ያደረጉት የተቋሙ የስልጠና እና አቅም ግንባታ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ክብረት ተቋሙ በሆቴልና ቱሪዝም ሙያ ዘርፍ በስልጠና፣ በምርምርና ማማከር እንዲሁም በቴክኖሎጂ ሽግግር ግንባር ቀደም ሆኖ መቀጠል የቻለው ከዘርፉ ባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር እና በቅንጅት ስለሰራ ነው ብለዋል።

ሰልጣኞች ተቋሙ የሚሰጠውን የንድፈሃሳብና የተግባር ስልጠና ሲያጠናቅቁ ወደ ኢንደስትሪ ተልከው ልምምድ እንዲያደርጉ የባለድርሻ አካላት ትብብር በእጅጉ አስፈላጊ ነው ብለዋል።
አቶ ሀብታሙ አክለውም በተቋሙ እየተተገበረ ስላለው የሪፎርም ሥራ ለባለድርሻ አካላት ግንዛቤ እንዲያገኙ በማድረግ ሪፎርሙ ለአሰልጣኞች፣ ለሰልጣኞች እንዲሁም ለተገልጋዮች ምቹ ሁኔታን እንደፈጠረ ገልጸዋል።
የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናውን የኢንስቲትዩቱ ቮኬሽናል ጋይዳንስ እና የትብብር ስልጠና ማስተባበሪያ ዲን አቶ ታደሰ ሞላ በትምህርት፣ ሳይኮሎጂ፣ ኮሚዩኒኬሽን እና ስነ ምግባር ላይ ሰፋ ያለ ገለፃ አድርገዋል።
በተጨማሪም ከምርታማነት ማሻሻያ የልህቀት ማዕከል የአቅም ግንባታ ዘርፍ ምክትል ዲን አቶ ተሾመ ፈይሳ ስለኢንዱስትሪ ማሰልጠን ስነ ዘዴ ስልጠና ሰጥተዋል።
በመጨረሻም የተቋማችን አሰልጣኝ አቶ ሳለአምላክ ፈንታ የትብብር ስልጠና የሚሰጡ ተቋማት እቅድ አወጣጥና የውጤት አሞላል ዙሪያ ስልጠና ተሰጥተዋል።
ከተሳታፊዎች መካከል አቶ ሙሉቀን ዘገዬ ከስካይላይት ሆቴልና አቶ ሙላቱ ወርቅዬ ከአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የጥናትና ምርምር ሙዚየም የተሰጠው ስልጠና ጠቀሜታውን በመግለፅ ተቋሙ በየጊዜው ለትብብር ሰልጠና የሚላኩ ሰልጣኞችን በሰለጠኑት ሙያ እንዲበቁ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ እንዳሚገባው ተናግረዋል።
ኢንስቲትዩቱ 30% የንድፈ ሃሳብ 70% የተግባር ስልጠና መርሃግብርን ይከተላል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et/