የባህላዊ ምግብ የፌስቲቫሉ ፋይዳ ከኢኮኖሚ ያለፈ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮሙፈሪሃት ካሚል ገለፁ፡፡በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት፣ ኩሪፍቱ ሪዞርት የአፍሪካ መንደር እና የሸገር ከተማ አስተዳደር ጋር በመተባበር የኢትዮጵያ ባህላዊ ምግቦች ፌስቲቫል መካሄድ ጀምሯል።

የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፣ በፌስቲቫሉ ከመላ የሀገራችን አካባቢዎች በጥናት ተለይተው የተመረጡ ባህላዊ ምግቦች ቀርበዋል፡፡
እነዚህ መግብቦች በብዛት ለበዓላት የሚቀርቡ ተወዳጅ፤ ነገር ግን እምብዛም ከጓዳ ያልወጡ ናቸው ብለዋል፡፡
የዚህ አይነትቱ መርሃ ግብር እንደዚህን እምቅ አቅሞች ከጓዳ ወደ አደባባ እንዲወጡ እንደሚያግዝም አመላክተዋል፡፡
ሂደቱም ለዜጎች ተጨማሪ የሥራ ዕድልና ሀብት የሚፈጥሩ ከማድረግ እና ኢትዮጵያ መልከ ብዙ መሆኗን በአግባቡ ከማስተዋወቅ ባሻገር የጋራ መግባባት እና ጠንካራ ሀገረ መንግስት ለመፍጠር ለምናደርገው ጥረት ፋይዳቸው የላቀ ነው ሲሉም አብራርተዋል፡፡
ይህ ሂደት ለእናቶች፣ ለሴቶች እና ለወጣቶች አዳዲስ ዕድሎችን የመፍጠር አቅሙ ከፍተኛ እንደሆነም ነው ክብርት ሚኒስትር ያመላከቱት፡፡
የባህላዊ ምግብ የፌስቲቫሉ ፋይዳ ከኢኮኖሚ ያለፈ መሆኑን ያነሱት ክብርት ሚኒስትር ሁሉንም የኢትዮጵያን መልኮችና ማንነቶች ወደፊት ለማምጣት በዚህ መልኩ ስንሰራ ከምንፈጥረው የሥራ ዕድል ባሻገር በዘላቂነት የኢትዮጵያን ሰላምና አንድነት ለማጽናጽና ኢትዮጵያን በሁለንተናዊ መልኩ ለማስተዋወቅ እድል ይፈጥራል ብለዋል፡፡
ጥቅምት 1/2018 ዓ.ም ፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
Official Website: mols.gov.et
Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE
Telegram: t.me/fdre_mols
TikTok: tiktok.com/@mols_official
Twitter / X: twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር
WhatsApp: whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtTbPZtDW1y