የሚኒስቴር መስሪያ ቤታችን ተጠሪ ተቋም የሆነው የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የዓለም አቀፍ የትምህርትና ስልጠና ሥራ አመራር ሥርዓት ማረጋገጫ አግኝቷል።
ይህ እውቅና ለኢንስቲትዩቱ ብቻ ሳይሆን፣ ለሀገራችን የክህሎት ልማትና የቱሪዝም ዘርፍም አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት ትልቅ ስኬት ነው።
ይህ ስኬት ኢንስቲትዩቱ ከዓለም አቀፍ ደረጃ ጋር የተጣጣመ የላቀ ሥልጠና፣ ምርምርና የማማከር አገልግሎት እንዲሰጥ ያስችለዋል። በተጨማሪም ዜጎች ከተቋሙ ቀልጣፋ፣ ተደራሽና ፍትሐዊ አገልግሎቶችን እንዲያገኙ ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል፡፡
እንደ ዘርፍ ለሥራው ልዩ ትኩረት የተሰጠ ሲሆን የሥራና ክህሎት ሚኒስቴርን ጨምሮ የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኢንስቲትዩትን እና የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩትን ጨምሮ ከ16 በላይ ተቋማት የዓለም አቀፍ የሥራ አመራር ስርዓት ማረጋገጫ ማግኘት ችለዋል።
በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አመራር የተጀመረው መንግሥት ለአገልግሎት ጥራትና ቅልጥፍና እንዲሁም ለፈጠራና ፍጥነት የሰጠውን ልዩ ትኩረት የሚያሳይ ነው።
የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት አመራርና ሠራተኞች ለስኬቱ ላደረጋችሁት ርብርብ እንዲሁም የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩትና የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት በዘርፉ እያደረጋችሁ ላለው ሁሉን አቀፍ ድጋፍ ሙያዊ ድጋፍ ከልብ የመነጨ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ፡፡
የሥራ ባለቤት እርስዎ ነዎት!

Recent Comments